በሞዛምቢክ ሰሜናዊ ክፍል 59 አሸባሪዎች መገደላቸውን የሀገሪቱ መከላከያ አስታወቀ
በሞዛምቢክ ሰሜናዊ ክፍል 59 አሸባሪዎች መገደላቸውን የሀገሪቱ መከላከያ አስታወቀ
በሞዛምቢክ ሰሜናዊ ግዛት 59 አሸባሪዎች በትናንትናው እለት መገደላቸውን የሞዛምቢክ መከላከያና የጸጥታ ኃይል ማስታወቁን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
መንግስት አሸባሪ ያላቸው አካላት ሞሲምቦ የተባለውን ግዛት በመውረርና ወደ አካባቢው ማህበረሰብ በመቀላቀል ጥቃት ለማድረግ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር የመከላከያ ኃይሉ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡
መከላከያው በወሰደው እርምጃ 59 የሚሆኑ አሽባሪዎች መገደላቸውንና ስድስት ካምፖች እስከመጠቀሚያ ቁሳቁሶቻቸው መውደሙን ተነግሯል፡፡ በመግለጫው መከላከያ ኃይሉ የሰለም ሁኔታውን ወደ ቀድሞው መልሷል፤ የመልሶ ማጥቃት በመስራት አሸባሪዎችን የማጥራት ስራ መስራቱንም ተጠቅሷል፡፡
መከላከያ ኃይሉ ማንኛውም ሰው የተለየ እንቅስቃሴ በተለይ የትጥቅ እንቅስቀሴ ሲያይ ለመንግስት በመጠቆም እንዲተባበር ጥሪ አቅርቧል፡፡