የሶማሊያ ጦር አልሸባብን “ማስወገድ” እንዳቃተው አሜሪካ ገለጸች
አልሸባብ ከ7ሺ እስከ 9 ሺ የሚደርስ አባላት እንዳሉት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሪፖርት ያሳያል
በአሜሪካ የሰለጠኑና የታጠቁ የሶማሊያ ወታደሮች የሚያካሂዷቸው ዘመቻዎች በተጠበቁት ልክ ውጤታማ አለመሆናቸው ተገልጿል
በአሜሪካ የሰለጠኑና የታጠቁ የሶማሊያ ወታደሮች የሚያካሂዷቸው ዘመቻዎች በተጠበቁት ልክ ውጤታማ አለመሆናቸው ተገልጿል
የሶማሊያ ጦር አልሸባብን ከምሽጉ ማስወገድ አቅም በማነሱና ባለመቻሉ ምክንያት ሰርጎገቦች ተለማምደው ሰፊ የሆነ የሀገሪቱን ግዛት ለመቆጣጠር እየሰሩ መሆኑን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትናንትናው እለት አስታውቋል፡፡
ከ13 አመታት የጸረ-ሰርጎገብ ጦርነት በኋላ ከልሸባብ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሀይሎች ባለፈው አመት ከ1000 በላይ ጥቃቶችን በሶማሊያና በሰሜን ኬንያ ማድረሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ በፈረንጎቹ “2019 የሀገራት የሽብርተኝነት ሪፖርት” ላይ ጠቅሷል፡፡
ሶማሊያን የሚመለከተው የሪፖርቱ ክፍሉ አልሸባብ ከ7ሺ እስከ 9 ሺ የሚደርስ አባላት አሉት ይላል፡፡
የአልሸባብ ገቢ ምንድነው?
አልሸባብ ህገወጥ ከሆነ ምርትና ሽያጭ፣ከአካባቢው ከሚገኘው ማህበረሰብ ግብርና የሶማሊያ ዲያስፖራዎች የሚልኩት ገንዘብ የሀብት ምንጩ መሆናቸውን ሪፖርት ይገልጻል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ አልሸባብ ምን ያህል ሰራዊት እንዳለው አልገለጸም፡፡
በአሜሪካ የሰለጠኑና የታጠቁ የሶማሊያ ወታደሮች የሚያካሂዷቸው ኢላማ ያላቸው ዘመቻዎች በተጠበቁት ልክ ውጤታማ አይደሉም ተብሏል፡፡ ነገርግን ሪፖርቱ በአፍሪካ የአፍሪካ ኮማንድ ስላካሄደው ዘመቻ ምንም ያለው ነገር የለም፡፡
ኮማንዱ ባለፈው አመት 63 የአየር ጥቃት ያደረሰ ሲሆን ይህም በፈረንጆቹ 2018 እና 2017 ከነበረው የአየር ጥቃት ዘመቻ ቁጥር ይበልጣም ብሏል ሪፖርቱ፡፡
እንደ ሪፖርቱ ከሆነ የሶማሊያ ባለስልጣናት ወሳኝ የብሄራዊ የጸጥታ ለውጥ ማድረግ አልቻሉም፤የመንግስትም ጸጥታ ማስከበር አቅም የሚያሳድግ ህግም ማውጣት አለመቻላቸውን ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡
ነገርግን የሶማሊያ መንግስት እስካሁን ከአሜሪካ ጋር ተባብሮ ለመስራት ፍቃደኛ መሆኑን ሪፖርቱ ገልጿል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሪፖርቱ ኬንያም አሽባሪዎችን በመመርመርና በመያዝ ከአሜሪካ ጋር እየተባበረች ነው ብሏል፡፡