የሶማሊያ ጦር 12 የአልሸባብ ታጣቂዎችን መግደሉን አስታወቀ
የሶማሊያ ጦር 12 የአልሸባብ ታጣቂዎችን መግደሉን አስታወቀ
የሶማሊያ ጦር በደቡባዊ ክልል በሚገኘው የታችኛው ሸበሌ ባደረገው ዘመቻ ባለፈው ሰኞ እለት 12 የአልሸባብ አክራሪ ታጣቂዎችን መግደሉን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
የሶማሊያ ልዩ ኃይል 16ተኛ ምድብ አዛዥ የሆነው እስማኤል አሊ ማሊክ በአልሸባብ ምሽግ ላይ ተኩስ በመክፈት ጉዳት ማድረሳቸውን ገልጸዋል፡፡
“ጥቃቱን በተሳካ ሁኔታ ማካሄድ ችለናል፡፡ በጦሩና በታጣቂዎቹ መካከል መፋጠጥ ነበር፤ ነገር ግን ጦሩ አሸንፎ 12 ታጣቂዎችን ገድሏል” ብለዋል፡፡
አዛዡ ጦሩ ታጣቂዎቹን ሙሉ በሙሉ ከክልሉ እስከሚያሶጣ ድረስ ጥቃቱ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
የአካባቢው ነዋሪዎች በመንግስት ታጣቂዎችና በአልሸባብ መካከል የነበረው የተኩስ ልውውጥ ማየታቸውን ተናግረዋል፡፡
የአልሸባብ ታጣቂዎች እ.ኤ.አ. በ2011 በሶማሊያና በአፍሪካ ህብረት ጥምር ጦር ከዋና ከተማዋ ሞቃዲሹ ከተባረሩ በኋላ በደቡባዊ ሶማሊያ ከመንግስት ጋር የሚያደርጉት ግጭት የተመደ ሆኗል፡፡