በሲዳማ ክልል ባጋጠመ የመንገድ የትራፊክ አደጋ ከ 70 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ፖሊስ አስታወቀ
ፖሊስ አደጋው የደረሰው ሰዎችን አሳፍሮ በና ከተባለ ቦታ ወደ በንሳ በመጓዝ ላይ የነበረ አይሱዙ ተሽከርካሪ ድልድይ ስቶ ገላና ወንዝ ውስጥ ገብቶ ነው ብሏል

ከአደጋው በህይወት የተረፉት በቦና አጠቃላይ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን የደቡብ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን አጄንሲ የክልሉን ኮሙኒኬሽን ቢሮ ጠቅሶ ዘግቧል
በሲዳማ ክልል ባጋጠመ የመንገድ የትራፊክ አደጋ ከ 70 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ፖሊስ አስታወቀ ።
የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ትናንት ምሽት በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ በክልሉ ምስራቃዊ ዞን በተፈጠረ የትራፊክ አደጋ ከ 70 በላይ ሰዎች መሞታቸውን አስታውቋል።
ፖሊስ አደጋው የደረሰው ሰዎችን አሳፍሮ በና ከተባለ ቦታ ወደ በንሳ በመጓዝ ላይ የነበረ አይሱዙ ተሽከርካሪ ድልድይ ስቶ ገላና ወንዝ ውስጥ ገብቶ ነው ብሏል።
ፖሊስ አክሎም በአደጋው ከሞቱት ውሰጥ ሶስቱ ሴቶች ናቸው። ብሔራዊው ቴሌቪዥን ኢቢሲ እንደዘገበው በመገልበጥ አደጋው የሞቱት ሰዎች ሰርገኞች ናቸው።
ከአደጋው በህይወት የተረፉት በቦና አጠቃላይ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን የደቡብ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን አጄንሲ የክልሉን ኮሙኒኬሽን ቢሮ ጠቅሶ ዘግቧል።