ብዙ መንገደኞች የተገደሉባቸው አስከፊ የዓለማችን አውሮፕላን አደጋዎች እነማን ናቸው?
በደቡብ ኮሪያ የበረራ አስተናጋጆችን ጨምሮ 181 መንገደኞች በተሳፈሩበት አውሮፕላን ላይ በደረሰ አደጋ ሁለት ሰዎች ብቻ በተዓምር ተርፈዋል
ከ23 ዓመት በፊት በአሜሪካ ዋሸንግተን በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ 3 ሺህ መንገደኞች የሞቱበት በታሪክ በገዳይነቱ ይጠቀሳል
ብዙ መንገደኞች የተገደሉባቸው አስከፊ የዓለማችን አውሮፕላን አደጋዎች እነማን ናቸው?
የአውሮፕላን ጉዞ ድካምን በመቀነስ፣ በፍጥነት ለመጓዝ እና ከምቾት አንጻር ተመራጭ የትራንስፖርት አማራጭ ቢሆንም አደጋዎች ካጋጠሙ ግን በገዳይነቱ ወደር የለውም፡፡
የበረራ አስተናጋጆችን ጨምሮ 181 ተሳፋሪዎችን ይዞ ከባንኮክ ተነስቶ ወደ ሙዓን ኤርፖርት ከደረሰ በኋላ ለማረፍ ሲሞክር በተፈጠረ አደጋ የ179 ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል፡፡
አደጋው በደቡብ ኮሪያ ታሪክ በገዳይነቱ ሁለተኛው አደጋ ሆኖ መመዝገቡ ተገልጿል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ በዓማችን በተለያዩ ከተከሰቱ የአውሮፕላን አደጋዎች ውስጥ ብዙ ሰዎች ያለቁበት በፈረንጆቹ መስከረም 11 ቀን 2001 ላይ የተከሰተው የዋሸንግተን አደጋ የመጀመሪያው ነው፡፡
የአልቃይዳ ሽብር ቡድን ሀላፊነት በወሰዱበት በዚህ አደጋ 3 ሺህ ገደማ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
ሁለተኛው ብዙ ሰዎችን የገደለው የአውሮፕላን አደጋ ደግሞ በዚሁ በአሜሪካ በ1977 በሮስ ሮዴስ ኤርፖርት ሁለት አውሮፕላኖች እርስ በርስ ተጋጭተው ለ583 መንገደኞች ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆኗል፡፡
1985 ላይ ከቶኪዮ ወደ ኦሳካ በመብረር ላይ እያለ ታካማጋራ ተራራ ላይ ተከስክሶ ለ520 መንገደኞች ሞት ምክንት የሆነው ተመሳሳይ አደጋ ደግሞ ሶስተኛው ገዳይ አደጋ ተብሎ ተመዝግቧል፡፡
በታሪክ በገዳይነታቸው አራተኛ ተብሎ የተመዘገበው የአውሮፕላን አደጋ ደግሞ ከህንድ ዴልሂ ወደ ሳውዲዋ ዳራን እየበረረ የነበረ አውሮፕላን ቻርኪ ዳድሪ ላይ ተከስክሶ 349 መንገደኞች ሞተዋል፡፡