በዲአርሲ በደረሰው የጀልባ መገልበጥ አደጋ 78 ሰዎች ሰጠሙ
ጀልባዋ 278 ሰዎች አሳፍራ እንደነበር የአካባቢው ባለስልጣን ተናግረዋል
ጀልባዎች ከአቅማቸው በላይ በሚጭኑባቸው በዲአርሲ ውሃማ አካላት ከባድ የመገልበጥ አደጋዎች የተለመዱ ናቸው
በዲአርሲ በደረሰው የጀልባ መገልበጥ አደጋ 78 ሰዎች መስጠማቸው ተገለጸ።
ቢያንስ 278 ሰዎች አሳፍራ የነበረች ጀልባ በምስራቃዊ ዲሞክራሲያዊ ኮንጎ ሪፐብሊክ (ዲአርሲ) በሚገኘው ኪቩ ሀይቅ ላይ ስትገለበጥ 78 ሰዎች መስጠማቸውን የግዛቱ አስተዳዳሪ ተናግረዋል።
በመስጥም አደጋ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች በአስከሬን መጠቅለያ ሲጫን የሰለባዎቹ ቤተሰቦች ሲያለቅሱ እንደነበር ሮይተርስ የአይን እማኞችን ጠቅሶ ዘግቧል።
እስካሁን ምን ያህል ሰው በትክክል እንደጠፋ እንደማይታወቅ እና የአካባቢው ባለስልጣናትም እርስበእርሱ የሚጣረስ ቁጥር እየሰጡ መሆናቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
የደቡብ ካቩ ግዛት ገዥ የማቾች ቁጥር 78 መሆኑን እና በአጠቃላይ በጀልባዋ ላይ ተሳፍረው የነበሩት 278 እንደነበሩ ገልጿል።
"ሁሉም አስከሬኖች ስላልተገኙ ትክክለኛ ቁጥሩን ለማግኘት ቢያንስ ሶስት ቀናት ይፈጃል" ሲሉ ገዥው ጂን ጃኩይስ ፑሪሲ ተናግረዋል።
የአጎራባች ሰሜን ኪቩ ግዛት ገዥ ደግሞ የሟቾች ቁጥር 58 መሆኑን እና እስካሁን 28 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ መረጋገጡን ገልጿል። ጀልባዋ የተገለበጠችው ከየብስ 700 ሜትር ርቀት መሆኑን የገለጸው ገዥው የአደጋው መንሰኤ እየተጣራው ነው ብሏል።
ጀልባዎች ከአቅማቸው በላይ በሚጭኑባቸው በዲአርሲ ውሃማ አካላት ከባድ የመገልበጥ አደጋዎች የተለመዱ ናቸው።