ሰሜን ኮሪያ ሉአላዊነቷ የሚጣስ ከሆነ በኑክሌር ጦር መሳሪያ ምላሽ እሰጣለሁ ስትል አስጠነቀቀች
ኪም ይህን አስተያየት የሰጡት በሀገሪቱ ጦር ልዩ ኃይል ማሰልጠኛ ጣቢያ በተገኙበት ወቅት ነው
ኪም እንደተናገሩት ዩን "የኑክሌር ጦር መሳሪያ በታጠቀች ሀገር ደጃፍ ሆኖ ወታደራዊ አቅም አለኝ ብሎ መዛቱ ጤነኝነቱን የሚያጠራጥር ነው" ብለዋል
ሰሜን ኮሪያ ሉአላዊነቷ የሚጣስ ከሆነ በኑክሌር ጦር መሳሪያ ምላሽ አሰጣለሁ ስትል አስጠነቀቀች።
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጅንግ ኡን ጠላት ሉአላዊነቷን የሚጥስ ከሆነ ኑክሌር የጦር መሳሪያን ጨምሮ በእጇ ያሉትን የጦር መሳሪዎች ከመጠቀም ወደ ኋላ እንደማትል ተናግረዋል።
ሮይተርስ የሰሜን ኮሪያውን ኬሲኤንኤ ቴሌቪዥን ጠቅሶ እንደዘገበው ኪም የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝደንት ዮ ሱክ የኦል በወታደራዊ ትርኢት ላይ የሰሜን ኮሪያውያን አገዛዝ ለማጥፋት መዛታቸውን ተችተዋል። ኪም ይህ አስተያየት ቀጠናዊ ሰላምን ማን እያናጋ እንደሆነ የሚያሳይ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ኪም እንደተናገሩት ዩን "የኑክሌር ጦር መሳሪያ በታጠቀች ሀገር ደጃፍ ሆኖ ወታደራዊ አቅም አለኝ ብሎ መዛቱ ጤነኝነቱን የሚያጠራጥር ነው" ብለዋል።
"ጠላት በአላዋቂነት እና በግዴለሽነት የጦር ኃይሉን ተጠቅሞ ድንበር የሚጥስ ከሆነ ሰሜን ኮሪያ የኑክሌር የጦር መሳሪያዎችን ጨምሮ በእጇ ያሉትን መሳሪያዎች በመጠቀም ምላሽ ለመስጠት አታመነታም" ሲሉ መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
እንደዘገባው ከሆነ ኪም ይህን አስተያየት የሰጡት በሀገሪቱ ጦር ልዩ ኃይል ማሰልጠኛ ጣቢያ በተገኙበት ወቅት ነው።
ሰሜን ኮሪያ ለበርካታ አስርት አመታት የኑክሌር ጦር መሳሪያ ፕሮግራሟን እያስቀጠለች ሲሆን በደርዘን የሚቆጠሩ የኑክሌር ጦር መሳሪያ ለማምረት የሚያስቸል በቂ 'ፊዝል' እንዳላት ይታመናል።
ሀገሪቱ በከመሬት በታች የተሰሩ ስድስት የኑክሌር ማበልጸጊያ ጣቢያዎች አሏት ተብሏል።
ደቡብ ኮሪያ ባለፈው ማክሰኞ አመታዊ የጦር ሰራዊት ቀኗን አስመልክታ ባቀረበችው ወታደራዊ ትርኢት ላይ ከባድ ተተኳሽ ያለው ባለስቲክ ሚሳይል እና የአሜሪካ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች ሲበሩ አሳይታለች።
ዩን ባሰሙት ንግግር ሰሜን ኮሪያ የኑክሌር ጦር መሳሪያ የምትጠቀም ከሆነ ከአሜሪካ ጋር በመሆን ጠንካራ ምላሽ እንደምትሰጥ አስጠንቅቀዋል።
"ያኔ የሰሜን ኮሪያን ፍጻሜ እናያለን" ብለዋል ዩን።
ኪም "የጠላቶች ማስፈራሪያ፣ ድርጊት እና ማጭበርበሪያ የሰሜን ኮሪያን ወታደራዊ አቅም ያላገናዘበ፣ የእኛን ኑክሌር ጦር መሳሪያ ሊወስድ የማይችል ነው" ማለታቸውን ተዘግቧል።