ባሳለፍነው አርብ በእስራኤል የተገደሉት ሀሰን ናስራላህ በሚስጥር መቀበራቸው ተገለጸ
ሂዝቦላህ መሪውን በሚስጥር የቀበረው የእስራኤል ጥቃትን በመሸሽ ነው ተብሏል
ሀሰን ናስራላህ በሚስጥራዊ ስፍራ በጊዚያዊ ቦታ ላይ ስርዓተ ቀብራቸው እንደተፈጸመ ተገልጿል
ባሳለፍነው አርብ በእስራኤል የተገደሉት ሀሰን ናስራላህ በሚስጥር መቀበራቸው ተገለጸ፡፡
በሐማስ ጦርነት ምክንያት ከፍልስጤማዊን ጎን በመቆም በእስራኤል ላይ ጥቃት ማድረስ የጀመረው ሂዝቦላህ መሪው ሀሰን ናስራላህ ከአንድ ሳምንት በፊት መገደላቸው ይታወሳል፡፡
በሊባኖስ መዲና ቤሩት የተገደሉት ሀሰን ናስራላህ ስርዓተ ቀብራቸው እስካሁን ሳይተወቅ የቆየ ሲሆን ብዙዎች ደጋፊዎቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት እንደሚካሄድ ጠብቀው ነበር፡፡
ይሁንና ሂዝቦላህ ለ32 ዓመታት ሲመሩ የነበሩት መሪውን ሚስጥራዊ በሆነ ቦታ ስርዓተ ቀብራቸውን እንደፈጸመ ተገልጿል፡፡
ሂዝቦላህ በእስራኤል የተገደሉበት አመራሩን በሚጥር ስርዓተ ቀብራቸውን የፈጸመው የእስራኤልን ጥቃት በመፍራት ነው፡፡
የሀሰን ናስራላህ ስርዓተ ቀብር ደጋፊዎቻቸው እና ሌሎች ዜጎች በተገኙበት በአደባባይ ቢፈጸም እስራኤል ጥቃት ልትፈጽም ትችላልች ተብሎ እንደተሰጋ የተገለጸ ሲሆን የተሻለ ጊዜ ሲገኝ ስርዓተ ቀብሩ በይፋ ይፈጸማል ተብሏል፡፡
በእስራኤል- ሄዝቦላህ ጦርት ምን አዳዲስ ክስተቶች ተስተናግደዋል?
ይህ በዚህ እንዳለ የእስራኤል አየር ሀይል ዛሬ ጠዋት ላይ ሀሺም ሰፌዲን አሉበት በተባለ ስፍራ ላይ የአየር ድብደባ ፈጽሟል፡፡
ከቤሩት ኤርፖርት አጠገብ ይገኛል የተባለው ይህ ሀሺም ሰፌዲን አሉበት የተባለው ስፍራ የእስራኤል ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች ተደጋጋሚ እና ከባድ ድብደባ እንዳደረጉ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ይሁንና ሂዝቦላህም ሆነ እስራኤል እስካሁን ሀሺም ሰፌዲን በጥቃቱ ኢላማ ስለመሆናቸው እና ስለመገደላቸው ያሉት ነገር የለም፡፡