81ኛውን የጀግኖች አርበኞች ድል በዓል አከባበር በፎቶ
ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅን ጨምሮ አባት አርበኞችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል
81ኛው የጀግኖች አርበኞች ድል ቀን በዓል ተከብሯል
81ኛው የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች የድል ቀን በዓል ተከብሯል፡፡
በዓሉ ኢትዮጵያውያን ጀግኖች አርበኞች ለዳግም ወረራ ከመጣው የፋሽስት ጣሊያን ወራሪ ሃይል ጋር ለአምስት ዓመታት ያህል በዱር በገደሉ ተዋድቀው ያስመዘገቡትን ደማቅ ለማሰብ የሚከበር ነው፡፡
ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ፣ የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል መስፍን ጆቴ እንዲሁም ሌሎች አባት አርበኞችና ባለስልጣናት በተገኙበት በአዲስ አበባ አራት ኪሎ ድል ሃውልት ስር የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥና በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ተከብሯል፡፡
በአከባበር ስነ ስርዓቱ የተለያዩ ሃገራት አምባሳደሮችና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ አባላት ተማሪዎች ወጣቶችና ታዳጊዎችም ተገኝተዋል፡፡
ይህን በማስመልከትም ዛሬ ማለዳ አስራ ሁለት ሰዓት ላይ 21 ጊዜ መድፍ መተኮሱ ይታወሳል፡፡
በ1928 ዓ/ም ወደ ኢትዮጵያን ዳግም ለመውረር የመጣው የፋሽስት ጦር በ1933 ዓ/ም ተመልሶ መውጣቱም አይዘነጋም፡፡