በአሜሪካ በቅዝቀዜ ምክንያት 90 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ
ከሟቾች ውስጥ አምስቱ የጎዳና ተዳዳሪዎች ናቸው ተብሏል
ቅዝቀዜውን ተከትሎም መዝናኛ ቤቶች በውሃ እና መብራት ችግር ምክንያት እየተዘጉ እንደሆነ ተገልጿል
በአሜሪካ 90 ሰዎች በቅዝቀዜ ምክንያት መሞታቸው ተገለጸ፡፡
በዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር አሜሪካ ባጋጠመ ቅዝቃዜ የዜጎች ህይወት ማለፉን ተከትሎ በሁለት በተወሰኑ ግዛቶች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅ ተገዳለች፡፡
ቅዝቃዜው በተለይም በደቡባዊ የሀገሪቱ አካባቢዎች የከፋ ሆኗል የተባለ ሲሆን በቴንሲ እና ኦሪጎን ግዛቶች ከ30 በላይ ዜጎች ህይወታቸው አልፏል ተብሏል፡፡
በ10 ሺህ የሚቆጠሩ አነሜሪካዊያንም ከመብራት አገልግሎት ውጪ ሆነዋል የተባለ ሲሆን በአጠቃላይ በመላው አሜሪካ 90 ሰዎች በቅዝቃዜ ምክንያት ህይወታቸው እንዳለፈ ተገልጿል፡፡
ከሟቾቾ ውስጥ አምስቱ በሲያትል የጎዳና ላይ ነዋሪዎች ናቸው የተባለ ሲሆን ሚሲሲፒ፣ ፔንሲልቫኒያ፣ ኒዮርክ እና ኒው ጀርሲ ግዛቶችም ቅዝቃዜው እየጨመረ እና ሰዎች እየሞቱ እንደሆነ ኤፒ ዘግቧል፡፡
በሚሲሲፒ ያሉ ዩንቨርሲቲዎች እና ኮሌጆችም ተማሪዎቻቸው በቅዝቃዜ እንዳይሞቱባቸው በሚል ወደ ቤተሰቦቻቸው የላኩ ሲሆን አስቀድመው ለእረፍት የሄዱትንም የመግቢያ ጊዜን አራዝመዋል፡፡
አሜሪካዊው ከ48 ዓመት እስር በኋላ በስህተት መታሰሩ ታወቀ
የውሃ ማሰራጫ መስመሮች በቅዝቃዜ ምክንያት በመፈንዳታቸው በተወሰኑ ግዛቶች የሚኖሩ በ100 ሺህ የሚቆጠሩ አሜሪካዊያን ውሃ እያገኙ እንዳልሆነም ተገልጿል፡፡
እንዲሁም እንደ ካፌ እና ሬስቶራንት ያሉ የመዝናኛ ቤቶች በውሃ እጥረት ምክንያት አገልግሎት መስጠት እያቆሙ ነውም ተብሏል፡፡
ስፖርታዊ ውድድሮችም በዚሁ ከባድ ቅዝቃዜ ምክንያት እየተራዘሙ እና ሙቀታማ ወደ ሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተዘዋወሩ እንደሆነም ተገልጿል፡፡