በትራምፕ የድጋፍ ሰልፍ ወቅት በነበረው ጥቃት ለቤተሰቦቹ ጋሻ በመሆን የሞተው ግለሰብ
ይህ ግለሰብ ኮሪ ኮምፕራቶር እንደሚባል ቤተሰቦቹ በፌስ ቡክ ገጻቸው ጽፈዋል
ኤፍቢአይ ጥቃቱን በማድረስ ተጠርጥሮ የተያዘው ግለሰብ ቶማስ ማቲው ክሩክስ የተባለ የ20 አመት ወጣት ነው ብሏል
በትራምፕ የድጋፍ ሰልፍ ወቅት በነበረው ጥቃት ቤተሰቦቹን የተከላከላ አንድ ሰልፈኛ በጥይት ተመቶ ህይወቱ አልፏል።
በትናንትናው እለት በፔንሲልቫኒያ በተካሄደው የዶናልድ ትራምፕ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ተኩስ በተከፈተ ወቅት የየ50 ከአመቱ በጎ ፈቃደኛ የእሳት አደጋ ሰራተኛ ለቤተሰቦቹ ጋሻ ሆኖ ህይወታቸውን ማትረፉን የግዛቷ ገዥ ጆሽ ሻፒሮ ተናግረዋል።
ይህ ግለሰብ ኮሪ ኮምፕራቶር ቤተሰቦቹ ቤተሰቦቹ በፌስ ቡክ ገጻቸው ጽፈዋል።
“ካልታሰበ ሞት ያዳነኝ የፈጣሪ ጥበቃ ብቻ ነው” - ትራምፕ
"የፔንሲልቫኒያው የትራምፕ ሰልፍ የወንድሜን የኮሬ ኮምፔራቶሬን ህይወት ቀጥፎብኛል። የአንድ ግለሰብ ጥላቻ ቤተሰቡን የሚወድ የአንድ ሰው ህይወት ቀጥፏል" ስትል የሟች እህት በትናንትናው እለት በፌስቡክ ገጿ ገልጻለች።
ኮምፔራቶራ ከዚህ በፊት የቡፋሎ ታውንሽፕ በጎ ፈቃደኛ የእሳት አደጋ ክፍል ባልደረባ እንደነበር ሮይተርስ የፒትስበርግ ፖስት ጋዜጣን ጠቅሶ ዘግቧል።
ሻፒዮ የኮምፔራቶሪን ቤተሰቦች በስልክ ማናገራቸውን ገልጿል።
"ኮሬ ጀግና ሆኖ ሞቷል። ትናንት ምሽት በነበረው ሰልፍ ኮሬ ዘሎ ቤተሰቦቹን አድኗል" ያሉት ሻፒሮ "ኮሬ የኛ ምርጣችን ነው" ሲሉ አክለዋል።
ኮምፔራቶሪ ባለትዳር እና የሁለት ሴት ልጆች አባት ነው።
"ኮሬ የሴት ልጅ አባት ነው። ኮሪ የእሳት አደጋ ተከላካይ ነው። እሁድን አዘውትሮ ወደ ቸርች ይሄዳል። ኮሬ የአካባቢውን ማህበረሰብ እና በተለይም ደግሞ ቤተሰቡን ይወዳል" ብለዋል ሻፒሮ።
ሻፒሮ ሰለባዎቹን የቀድሞው ፕሬዝደንት ቁርጠኛ ደጋፊ ሲሉ ገልጸዋቸዋል።
የተኩስ ድምጽ የተሰማው ፕሬዝደንት ትራምፕ ንግግር ማድረግ እንደጀመሩ ነበር። በዚህ ተኩስ ትራምፕም የቀኝ ጆሯቸው ተመትቶ በጸጥታ ኃይሎች አማካኝነት በፍጥነት ከመድረጉ እንዲወርዱ ተደርገዋል።
መንግስት በትራምፕ ላይ የተቃጣ የመግደል ሙከራ ሲል የጠራውን ይህን ጥቃት ያደረሰው ከፔንስልቬንያ ቤቴል ፓርክ የመጣ ቶማስ ማቲው ክሩክስ የተባለ የ20 አመት ወጣት መሆኑን የአሜሪካ የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ (ኤፍቢ) ለይቷል።
የአሜሪካ ፕሬዝደንኒ ጆ ባይደን "የአሜሪካ ዲሞክራሲ ቦታ የለውም" ሲሉ ጥቃቱን አውግዘዋል። ባይደን አሜሪካውያን እንዲረጋጉ እና በአንድነት እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።