በህይወት መኖሩን ለማረጋገጥ ተማሪዎችን ከነ መምህራቸው ያገተው ሰው
ግለሰቡ በስህተት በመንግስት እንደሞተ ተደርጎ መመዝገቡ እንዲሰረዝለት ቢጠይቅም የሚሰማው አጥቶ ነበር
በመጨረሻም ፖሊስ ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ በህይወት መኖሩን ለመመዝገብ ተገዷል
በህይወት መኖሩን ለማረጋገጥ ተማሪዎችን ከነ መምህራቸው ያገተው ሰው
ባቡራም ብሂል የተባለው ህንዳዊ የ40 ዓመት ጎልማሳ ራጃስታን በተሰኘችው ግዛት የሚኖር ሰው ነው፡፡
የግዛቲቱ አስተዳዳሪዎች ይህንን ሰው መሞቱን የሚያትት ማስረጃ ለቤተሰቦቹ ይልካሉ፡፡ በህይወት እያለ መሞቱን የሚያስረዳ ማስረጃ የደረሰው ይህ ሰው አለመሞቱን ለማሳየት ወደ ተቋሞ ቢሄድም የሚሰማው ያጣል፡፡
መንግስት ለግለሰቡ የሞት ማስረጃ ከሰጠ በኋላ ንብረቶቹ ወደ ሌላ ሰው ሊያስተላልፍ እንደሚችል የሰጋው ባቡራም በህይወት መኖሩን ለማሳየት መላ ይዘይዳል፡፡
ይህ ግለሰብም ባሳለፍነው ሳምንት ቢላዋ እና ቤንዚን ነዳጅ በመያዝ ባቅራቢያው ወዳለ አንደኛ ትምህርት ቤት ያመራል፡፡
ትምህርት ቤቱ ውስጥ ከገባ በኋላም በትምህርት ለይ ወደ ነበሩ አንድ ክፍል ድንገት በመግባት ተማሪዎቹን ከነ መምህራኑ ያግታል፡፡
የኢትዮጵያ ሰራተኞች በእገታ እና ጦርነት ምክንያት ከባድ ህይወት እያሳለፉ መሆናቸውን ኢሰማኮ ገለጸ
ተማሪዎች ከነ መምህራቸው ባልታወቀ ሰው መታገታቸውን ጥቆማ የደረሳቸው ፖሊሶችም ወደ ስፍራው ያመራሉ፡፡
በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው ይህ በህይወት የለም የተባለው በመጨረሻም ድርጊቱን የፈጸመው አለመሞቱን ለማሳየት በሚል እንደሆነ ይናገራል፡፡
በመጨረሻም ሞቷል በሚል በስህተት ተመዝግቦ የነበረው ሰው በህይወት መኖሩን አረጋግጧል ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡፡፡
ይሁንና ግለሰቡ ለፈጸመው ወንጀል መቀጣቱ እንደማይቀር በፖሊስ ተነግሮታል ተብሏል፡፡