ፖለቲካ
ፕሬዘዳንት ቡሃሪ የአሸባሪዎች እገታን ለመከላከል የጸጥታ ሃይሉን እንደገና እንደሚያደራጁ ገለጹ
ከሰሜናዊ ናይጀሪያ ታፍነው የተወሰዱ 300 ተማሪዎች ተለቀዋል ተብሏል
በናይጀሪያ እየጨመረ ያለውን ሽብር ለመከላከል የጸጥታ ሃይሉን እንደገና እንደሚያደራጁ ፕሬዘዳንቱ ገለጹ
የናይጀሪያው ፕሬዘዳንት ሙሃምደ ቡሃሪ የአዲስ አመት መልእክት ባስተላለፉበት ወቅት የጸጥታ ሃይሉን አቅም በመገንባትና ወታደሩን እንደገና በማደራጀት ላይ ትኩረት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡
ፕሬዘዳንቱ ይህን መልእክት ያስተላለፉት በሀገሪቱ የሽብር ጥቃት እየጨመረ በመጣበት ወቀት መሆኑን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
ቡሃሪ እንዳሉት በፈረንጆቹ 2021 ባለስልጣናት በተለይም እገታን፣ሽብርንና አመጽ የተቀላቀለበትን ወንጅል ለመከላከል ይሰራሉ፤ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሻሻልና ሙስናን ለመከላከል ይሰራሉ ብለዋል፡፡
በናይጀሪያ በአብዛኛው አካባቢዎች በታጣቂዎች የሚደረግ እገታ ባለፉት ሶስት ወራት የጨመረ ሲሆን በሰሜን ናይጀሪያ ደግሞ ቦኮሀራምን ጨምሮ በሌሎች አሸባሪዎች እየታመሰ እንደሚገኝ ተዘግቧል፡፡
ፕሬዘዳንት ቡሃሪ እንዳረጋገጡት ከሰሜናዊ ናይጀሪያ ካሲና ግዛት ከሚገኝ ትምህርት ቤት ታፍነው የነበሩ 300 ተማሪዎች መለቀቃቸውን ያረጋገጡ ሲሆን በዚህም ናይጀሪያ ወሳኝ በሆነ መልኩ ሽብርን መግታት እንደምትችል ያሳያል ተብሏል፡፡