የቀድሞ ፍቅረኛውን ለመበቀል ሲል መኖሪያ ቤቷን በምግብ ቤቶች ያስወረረው ሰው
ተከድቻለሁ ያለ ፍቅረኛ በከተማው ወዳሉ ምግብ ቤቶች ስልክ በመደወል ምግብ አዞላታል
ምግብ እንዲያደርሱ የታዘዙት ምግብ ቤቶችም አካባቢውን በትኩስ ምግብ ሽታ ከማወዳቸው ባለፈ ክፍያ ክፈይን አምባጓሮ ፈጥረዋል ተብሏል
የቀድሞ ፍቅረኛውን ለመበቀል ሲል መኖሪያ ቤቷን በምግብ ቤቶች ያስወረረው ሰው
ስሙ ያልተጠቀሰ የቱርኩ ሰው በፍቅረኛው መከዳት አጋጥሞታል ተብሏል፡፡ ይህ ሰው ፍቅሩን መቀጠል ቢፈልግም ባልተጠቀሰ ምክንያት ከፍቅረኛው ጋር እንደተለያየ ተገልጿል፡፡
በፍቅረኛው ውሳኔ የተበሳጨው ይህ ግለሰብ ፍቅረኛው የምትኖርበትን መንደር በምግብ ቤቶች አስወርሯል ተብሏል፡፡
ፍቅረኛው ከእሱ ጋር እንድትቀጥል የቻለውን ሁሉ ቢያደርግም እቅዱ ሳይሳካለት የቀረው ይህ ግለሰብ የበቀል እቅድ እንዳዘጋጀ ተገልጿል፡፡
ይህ በፍቅረኛዬ ተከዳሁ የሚለው ግለሰብ በኢስታምቡል ከተማ ወዳሉ ምግብ ቤቶች ስልክ በመደወል ምግብ ወደ መኖሪያ ቤቱ እንዲያመጡለት ያዛል፡፡
ይሁንና ምግብ እንዲያደርሱ የታዘዙት ምግብ ቤቶችም የታዘዙትን ምግቦች እንዲያመጡ የተነገራቸው አድራሻ የእሱ ሳይሆን ከዳችኝ ወዳላት የቀድሞ ፍቅረኛ መኖሪያ ቤት ነበር፡፡
የፍቅረኛውን መጸዳጃ ቤት እቃ ሰርቆ የተሰወረው ሰው
የፍቅረኛው መኖሪያ ቤትም በከተማዋ አሉ በተባሉ ምግብ ቤቶች የተጥለቀለቀች ሲሆን አካባቢውም በትኩስ ምግብ ሽታ እንዲታወድ ሆኗልም ተብሏል፡፡
በፍቅረኛዬ ተከዳሁ የሚለው የዚህ ሰው ድርጊት ትኩረት የሳበው ሰፈሩን በምገብ ቤቶች ከማስወረሩ ብቻ ሳይሆን የታዘዙትን ምግቦች ዋጋ ራሷ ፍቅረኛው ትክፈል ማለቱ ነው፡፡
ምግብ ቤቶቹም ይህችን እንስት የታዘዝነውን ምግብ ተቀበይን ሂሳባችንንም ከነ ማድረሻ ዋጋው ክፈይን ብለው አምባጓሮ ፈጥረዋልም ተብሏል፡፡