የፍቅረኛውን ምስል ያለፈቃዷ ለብዙዎች ያጋራው ሰው 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር እንዲከፍል ተቀጣ
ግለሰቡ ፍቅረኛውን ለመበቀል ሲል የእርቃን ፎቶዎችን ከፈቃዷ ውጪ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ አጋርቷል ተብሏል
ፎቶዎቿ በበርካታ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የተጋሩባት እንስት የስነ ልቦና ጉዳት ደርሶብኛል በሚል ክስ መመስረቷ ተገልጿል
የፍቅረኛውን ምስል ያለፈቃዷ ለብዙዎች ያጋራው ሰው 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር እንዲከፍል ፍርድ ቤት ወስኖበታል።
ግለሰቡ ፍቅረኛውን ለመበቀል ሲል የእርቃን ፎቶዎችን ከፈቃዷ ውጪ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ አጋርቷል ተብሏል
ፎቶዎቿ በበርካታ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የተጋሩባት እንስት የስነ ልቦና ጉዳት ደርሶብኛል በሚል ክስ መመስረቷ ተገልጿል።
የፍቅረኛውን ፎቶዎች ያለፈቃዷ ለብዙዎች ያጋራው ሰው 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር እንዲከፍል
በአሜሪካዋ ቴክሳስ ግዛት የቀድሞ ፍቅረኛውን ፎቶዎች በተለያዩ መንገድ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ያጋራው ሰው ቅጣት ተጥሎበታል።
ግለሰቡ ፍቅረኛውን የነበረችን እንስት ለምን ተለየሽኝ በሚል ምክንያት አብረው በፍቅር በቆዩባቸው ጊዜያት የተላላኳቸውን ምስሎች በመጠቀም ማስፈራራቱ ተገልጿል።
በዚህም ምክንያት የቀድሞ ፍቅረኛውን ፎቶዎች በማህበራዊ ትስስር ገጾች ያለፈቃዷ በማጋራቱ ክስ ተመስርቶበታል ተብሏል።
የእኔን እና የቤተሰቦቼን ፎቶዎች ያለ እኔ ፈቃድ በማክበራዊ ትስስር ገጾች በማጋራቱ የተለያዩ የስነ ልቦና ጉዳት እንደደረሰባት አስታውቃለች።
ለደረሰብኝ የስነ ልቦና ጉዳት ካሳ ይከፈለኝ በሚል ክስ የመሰረተችው ይህች እንስት የቴክሳስ ፍርድ ቤት 200 ሚሊዮን ዶላር ለስነ ልቦና ጉዳት በካሳ መልክ እንዲከፈላት ወስኗል።
እንዲሁም ድርጊቱን የፈጸመው ግለሰብ አንድ ቢሊዮን ዶላር ለፈጸመው ድርጊት መቀጣጫ እንዲሆን ቅጣት ተጥሎበታል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
በአሜሪካ በዓመት 10 ሚሊዮን ሰዎች ጾታዊ ጥቃት ይደርስባቸዋል የተባለ ሲሆን እድሜያቸው ከ18 እስከ 29 ዓመት የሆናቸው ዋነኛው የጥቃቱ ሰለባ ናቸው ተብሏል።