ልዩልዩ
የፍቅረኛውን መጸዳጃ ቤት እቃ ሰርቆ የተሰወረው ሰው
የቧንቧ ጥገና ባለሙያ የሆነው ይህ ግለሰብ ፍቅረኛው መለያየት እንደምትፈልግ ከነገረችው በኋላ እቃውን ይዞ ተሰውሯል ተብላል
እንስቷም የቅድሞ ፍቅረኛዬ የሚወደውን ነገር ሰርቆኝ ሄዳል ብላለች
የፍቅረኛውን መጸዳጃ ቤት እቃ ሰርቆ የተሰወረው ሰው
ከሰሞኑ በሀገረ አሜሪካ ፍቅረኛሞች በነበሩ ሰዎች መካከል የተፈጠረው ክስተት ብዙዎችን አስገርሟል።
በሴቷ ቤት አብረው እንደሚኖሩ እና ስማቸው ያልተጠቀሱት እነዚህ ፍቅረኛሞች በተለይም እንስቷ በቧንቧ ጥገና ሙያ የሚተዳደረው ፍቅረኛዋ ጋር ባለመግባባቷ ምክንያት መለያየት እንደወሰነች ትነግረዋለች።
በፍቅረኛው ውሳኔ የተበሳጨው ይህ ግለሰብም ፍቅረኛው እንደተኛች እቃውን ሸክፎ ከቤት እንደወጣ ሚረር ዘግቧል።
ዘገባው አክሎም ይህ ግለሰብ ከሻንጣው ጋር አብሮ የፍቅረኛውን መጸዳጃ ቤት ወይም በተለምዶ "ሲንክ" የተሰኘውን ቁሳቁስ ይዞ ተሰውሯል ብሏል።
ይህች እንስት የገጠማትን ክስተት በማህበራዊ ትስስር ገጿ ላይ ባጋራችው ጽሁፍ "የቀድሞ ፍቅረኛዬ የመጸዳጃ ቤት እቃዬን ነቅሎ ወስዷል፣ በገጠመኝ ነገር ልሳቅ ወይስ ላልቅስ" ስትል ጽፋለች።
"አውቃለሁ ህጋዊ የቧንቧ ጥገና ፈቃድ ያለው ባለሙያ ስለሆነ ይህን ማድረግ ቀላል ነው፣ አልዋሽም ፍቅረኛዬ ያደረገው ነገር አስቆኛል" ስትልም አክላለች።
የሁለቱ ፍቅረኞች ግንኙነት የተቋጨበት መንገድ አነጋጋሪ መሆኑ የቀጠለ ሲሆን ጉሳዩ በማህበራቂ ትስስር ገጾች ላይ ትኩረትን ስቧል።