የታዋቂው ሰዓሊ ፓብሎ ፒካሶ ፍቅርኛ በ101 ዓመታቸው አረፉ
ሰዓሊ ፓብሎ ፒካሶ የተለያቸው ሶስት የቀድሞ ፍቅረኞች ራሳቸውን አጥፍተዋል ተብሏል
ሰዓሊ ፒካሶ ከቀድሞ ፍቅረኛው ሁለት ልጆችን ወልደዋል
የታዋቂው ሰዓሊ ፓብሎ ፒካሶ ፍቅርኛ በ101 ዓመታቸው አረፉ፡፡
ፈረንሳዊቷ ፍራንሲስ ዥሎ በስዕል ስራው በዓለም ታዋቂ ከሖነ ጣልያናዊው ፓብሎ ፒካሶ ጋር የ21 ዓመት ወጣት እያለች ነበር የተዋወቁት፡፡
ዥሎ እና ሰዓሊ ፒካሶ የተዋወቁት በ60ዎቹ እድሜ ላይ እያለ ሲሆን በፍቅር በቆዩባቸው ዓመታት ሁለት ልጆችን ማፍራታቸው ተገልጿል፡፡
የስዕል ባለሙያ የሖነችው ዥሎ በ101 ዓመቷ በአሜሪካ ኒዮርክ ባለው መኖሪያ ቤቷ ህይወቷ ማለፉን ልጇ ኦውሪላ ኤንጅል ለኤፒ ተናግራለች፡፡
ታዋቂው የዓለማችን ሰዓሊ ፓብሎ ፒካሶ እና ዥሎ በፈረንጆቹ 1949 ላይ የተገናኙ ሲሆን በፍቅር በቆዩባቸው ጊዜያቶች ሁለት ልጆችን እንዳፈሩ ተገልጿል፡፡
ዥሎ እና ፒካሶ የመጋባት እቅድ ቢኖራቸውም ከሌላ ሴት ጋር ወስልቶብኛል በሚል ምክንያት ጋብቻቸው እና ፍቅራቸው ሳይሰምር ቀርቷል፡፡
ዥሎ በወቅቱ ከፍቅረኛዋ ጋር መለያየቷን አስመልክቶ ለሚዲያዎች እንዳለችው “ፓብሎ የህይወቴ ዋነኛው ፍቅሬ ነው፣ ነግር ግን ራሴን ለመጠበቅ ስል እና ከመጥፋቴ በፊት ተለያቼዋለሁ” ብላለች፡፡
ዥሎ አክላም የፓብሎ ፒካሶ የቀድሞ ሶስት ፍቅረኞች እና ሁለት ሚስቶች ፍቅራቸውን ሲያጡ ራሳቸውን አጥፍተዋል ሁለቱ ደግሞ በከባድ ጭንቀት ምክንያት ህይወታቸው ተጎድቷል፣ እኔ ግን ይህ እንዲሆን ባለመፈለጌ ትቼዋለሁ ብላም ነበር፡፡
ሀገሯ ፈረንሳይ በናዚ ጀርመኖች አጅ በወደቀችበት ወቅት የስዕል ኢግዚቢሽን በማሳየት ላይ እያለች ፓብሎ ፒካሶን የተዋወቀች ሲሆን በአውሮፓ እና በአሜሪካ ታዋቂ ሰዓሊ ለመሆን መብቃቷም ተገልጿል፡፡