ሩሲያዊው ጠፈርተኛ 1 ሺህ ቀናትን በህዋ ላይ በመቆየት የመጀመሪያው ሰው ሆነ
ጠፈርተኛው ከ2008 ጀምሮ 5 ጉዞዎችን ያደረገ ሲሆን በርካታ ቀናትን በህዋ ላይ በማሳለፍ ክብረወሰኑን ይዟል
አሜሪካ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ሩስያ በጠፈር ሳይንስ ላይ የሚያደርጉት ፉክክር እያደገ መጥቷል
ሩሲያዊው ጠፈርተኛ ኦሌግ ኮኔንኮ 1ሺህ ቀናትን በህዋ ላይ በማሳለፍ የመጀመርያው ሰው ተብሏል፡፡ ከ2008 ጀምሮ ወደ ህዋ መጓዝ የጀመረው ኮኔንኮ እስካሁን 5 ጉዞዎችን ወደ ጠፈር አድርጓል፡፡
ለመጨረሻ ግዜ በመስከረም 15 2023 ወደ ህዋ የተጓዘው ጠፈርተኛው ስራውን አጠናቆ ወደ ምድር የሚመለሰው በመጭው መስከረም 23 2024 ነው፡፡
ኮኔንኮ ወደ ምድር ሲመለስ እስካሁን በህዋ ከቆየባቸው ቀኖች ጋር ሲደመር በአጠቃላይ 1 ሺህ 110 ቀናትን በማሳለፍ የመጀመሪያው ሰው ይሆናል፡፡
ከዚህ ቀደም ረጅም ቀናትን በህዋ ላይ የቆየው ሌላኛው ሩስያዊ ጠፈርተኛ ጌናዲ ፓዳልካ ሲሆን ኮኔንኮ ባሳለፈነው ጥር ወር ላይ 878 ቀን ከ11 ሰአታት ከ29 ደቂቃ በመቆየት የዚህን ጠፈርተኛ ሪከርድ አሻሽሎታል፡፡
ጠፈርተኛው "ይህን አይነት ክብረወሰን በመያዜ ደስተኛ ነኝ በህዋ ላይ ይህን ያህል ጊዜ መቆየት ቀላል አይደለም ነገር ግን ስኬታማ በመሆኔ ደስተኛ ነኝ" ብሏል፡፡
አሜሪካ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ሩስያ ጠፈር ላይ የሚያደርጉት ፉክክር እያደገ መጥጧል፤ ሀገራቱ በግል እና በመንግስት ተቋማት የህዋ አዳዲስ ግኝቶችን በማስተዋወቅ እና የተለያዩ ሙከራዎችን በማድረግ እየተፎካከከሩ ይገኛሉ፡፡
ቲክቶክን ወደ ጠፈር የወሰደችው ጣሊያናዊቷ ጠፈርተኛ
ከሰሞኑም ቻይና በጨረቃ ላይ ከዚህ ቀደም ተደርሶባት በማይታወቅ ስፍራ ሰው አልባ መንኮራኩሯን ማሳረፏን ማስታወቋ ይታወሳል፡፡ ትላንት ደግሞ ከጨረቃ ናሙናዎችን የያዘችው መንኮራኩር ወደ ምድር ጉዞ መጀመሯ ተነግሯል፡፡
ህንድ ባሳለፍነው አመት በጨረቃ ደቡባዊ ዋልታ የጠፈር መንኮራኩር በማሳረፍ የመጀመሪያዋ ሀገር መሆን ችላለች።
ቻንድራያን-3 የተሰኘችው መንኮራኩር የውሃ ክምችት ሊኖርበት ይችላል በተባለው የጨረቃ ክፍል በሰኬት ማረፍ መቻሏን አስታውቃ ነበር፡፡
ህንድን በመከተል ከ6 ወራት በኋላ አሜሪካ ከ50 አመታት ወዲህ ለመጀመርያ ግዜ መንኮራኩሯን በጨረቃ ደቡብ ዋልታ ላይ ማሳረፍ መቻሏ ይታወሳል።