ራስዎን ከማያውቁት ሰው ጋር ጋብቻ መስርተው ቢያገኙት ምን ይላሉ?
ከሶስት ዓመት በፊት ፓስፖርቷ የጠፋባት ሴት በመጨረሻም አይታው የማታውቀው ሰው ሚስት ሆና ተገኝታለች
በሩሲያዋ ፒተርስበርግ ከተማ የምትኖረው ይህች ሴት መንግስት ሙስጠፋ የተባለ ግብጻዊ ሰው አግብተሻል ብሎ መዝግቦት ተገኝቷል
ራስዎን ከማያውቁት ሰው ጋር ጋብቻ መስርተው ቢያገኙት ምን ይላሉ?
በሩሲያ ፒተርስበርግ ከተማ የምትኖር አንድ የ24 ዓመት ሩሲያዊት ወደ አንድ የመንግስት ተቋም ለአገለግሎት ጎራ ስትል ባልሽ ካልመጣ አገልግሎቱን አታገኚም ትባላለች፡፡
ይህች ሴትም እንዳላገባች እና ባል እንደሌላት ብትናገርም አገልግሎቱን ለማግኘት የግድ አሁንም ባለቤቷ አብሯት መኖር አልያም ውክልና መያዝ እንዳለባት ይነገራታል፡፡
ከብዙ ክርክር በኋላም ሙስጠፋ የተባለ ግብጻዊ ሚስቱ እንደሆነች ይህ ሰውም ሩሲያዊት በማግባቱ ምክንያት በፒተርስበርግ ከተማ የመኖሪያ ፈቃድ ተሰጥቶት እንደሚኖር ትረዳለች፡፡
ይሁንና ይህች ሴት የተባለውን ሰው እንደማታውቀው፣ ጋብቻም እንዳልመሰረተች ለመንገስት ተቋማት ማሳወቋን ተከትሎ ጉዳዩ መመርመር ይጀምራል፡፡
በመጨረሻም ይህ ግብጻዊ የሩሲያዊቷን ፓስፖርት በህገወጥ መንገድ እጁ ላይ በማስገባቱ ጋቻ የመሰረተ በማስመሰል የሩሲያ መኖሪያ ፈቃድ ሊያገኝ ችሏል ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡
የጋብቻ ጥያቄ የተቀበለችው የናይጄሪያ ወታደር ታሰረች
በመጨረሻም የዚች ሴት ጋብቻ በሩሲያ ፍርድ ቤት እንዲሰረዝ ተደርጓል የተባለ ሲሆን ሁለቱም ተጋቢዎች በአካል ሳይቀርቡ እንዴት ጋብቻው ተፈጸመ የሚለው ጥያቄ እስካሁን ምላሽ አላገኘም፡፡
እንዲሁም ወጣቷ ሩሲያዊት ፓስፖርቷ እንደጠፋባት ከሶስት ዓመት በፊት አመልክታ እያለ ጋብቻው እንዴት ህጋዊ ተደርጎ ተመዘገበ የሚለውም ሌላኛው ያልተመለሰ ጥያቄ ሆኗል፡፡
የሀገሪቱ ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡