ወታደሯ በሕግ ቁጥጥር ስር የዋለችው የደንብ ልብስን ለብሶ “መሞላቀቅ” የሚከለክውን መመሪያ በመጣሷ ነው
የናይጄሪያ ወታደር በስራ ላይ እያለች የቀረበላትን የ”ታገቢኛለሽ ወይ” ጥያቄ በመቀበሏ መታሰሯን የሀገሪቱጦር አስታወቀ።
የናይጄሪያ ጦር ቃል አቀባይ “ወታደሯ በስራ ላይ ሳለች የጋብቻ ጥያቄውን በመቀበሏ፤ የጦሩን የስነ ምግባር ደንብ ጥሳለች” ሲሉ ገልጸዋል።
የናጄሪያ ጦር አባል የሆነችው ወታደሯ በሕግ ቁጥጥር ስር የዋለችው የደንብ ልብስን ለብሶ መሞላቀቅ ክልክል በመሆኑ ነው ተብሏል።
ከወታደሯ ፊት ቀለበት የያዘ ግለሰብ ተንበርክኮ የታገቢኛለሽ ጥያቄ ላቀረበላት ፍቅረኛዋ የጋብቻ ጥያቄውን መቀበሏ ተገልጿል።
ወታደሯ ጋብቻውን መቀበሏን የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ቪዲዮ ባለፈው ሳምንት ተሰራጭቶ ነበር ተብሏል። ወንድ ወታደሮች ሙሉ የወታደር ደንብ ልብስ ለብሰው ፍቅራቸውን ሲገላለጹ እንደዚህ አይነት እርምጃ አለመወሰዱን ውሜን ኢምፓወርመንት እን ሌጋል ኤይድ የተባለ ቡድን ገልጿል።
በመሆኑም በወታደሯ ላይ የተወሰደዉ እርምጃ አድሎ እንዳለበትና እርሷን የማግለል ሁኔታ እንደሆነ የሴት የመብት ተሟጋች ድርጅቶች መናገራቸውን ያሆ ኒውስ ዘግቧል።
የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና በአንድ ወቅት ፕሬዝዳንታዊ ዕጩ የነበሩት ኦሞየሌ ሶዌሬ ጦሩ በወታደሯ ላይ ያሳለፈው ውሳኔ ትክክል አይደለም በማት አውግዘዋል።
ወታደሯ የጋብቻ ጥያቄውን የተቀበለችው መቼ እንደሆነ ባይታወቅም የተፈጸመው ግን በምዕራብ ማይጄሪያ ክዋራ ግዛት ነው ተብሏል።
በርካታ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ተከታታዮች ጥንዶቹን “እንኳን ደስ ያላችሁ” ሲሉ እንደነበር ተገልጿል። ሌሎች ደግሞ ወታደሯን ለማናደድ መሞከራቸው ተሰምቷል።
ወታደሯ የጋብቻ ጥያቄውን የተቀበለችው በመንግስት ወጣቶች የስልጠና ቦታ ነውም ተብሏል።