የአዕምሮ ጤና ባለሙያዎች ሊረዷት ቢሞክሩም እስካሁን መፍትሔ አላገኘሁም ብላለች
ለ11 ዓመታት እንቅልፍ ያልተኛችው እንስት
በእስያዊቷ ቬትናም ኩዋንግ ንጋይ በተሰኘች ከተማ የምትኖረው ትራን ቲ ሉ የተሰኘችው እንስት እንቅልፍ ከተኛች 11 ዓመት እንደሆናት ተናግራለች፡፡
ከ11 ዓመት በፊት እንደ ማንኛውም ጤነኛ ሰው እንቅልፍ ይወስደኝ ነበር የምትለው ይህች እንስት ማታ ተኝቼ ጠዋት ላይ በጉትጎታ ከእንቅልፌ የምነቃ ሰውም ነበርኩ ብላለች፡፡
ይሁንና ምክንያቱን በማላውቀው መልኩ ድንገት አይኔ እንባ ማፍሰስ ጀመረ፣ አይኔን ስጨፍንም እንባዬ ሊቆም አልቻለም ከዚያም እንቅልፍ መተኛት አቆምኩ ስትል ከሰሞኑ ለሀገሪቱ ቴሌቪዥን ተናግራለች፡፡
የ36 ዓመት እድሜ ያላት ይህች እንስት ህክምና ለማግኘት ወደ ሆስፒታል ማምራቷን እና ህክምና ለማግኘት መጣሯንም ተናግራለች፡፡
ለ60 አመታት እንቅልፍ በአይኔ አልዞረም የሚሉት የ80 አመት አዛውንት
የአዕምሮ ወይም ስነ ልቦና ጤና ባለሙያዎች የከፋ የእንቅልፍ ማጣት ወይም ኢንሶምኒያ ህመም አለብሽ ብለው እንደነነገሯትም ገልጻለች፡፡
እንቅልፍ የማጣት ህመም በህክምና ባለሙያዎች አማካኝነት በሚሰጥ ህክምና የሚድን የአዕምሮ ህመም ቢሆንም በተደጋጋሚ በተደረገልኝ ህክምና መዳን አልቻልኩም ብላለች፡፡
እንቅልፍ ባለመተኛቷ ምክንያትም ለተለያዩ ህመሞች ተዳርጌያለሁ የምትለው ይህች እንስት የትኩረት ማጣት፣ ወገብ ህመም እና የገጣጠሚያ ህመሞች እያሰቃዩኝ ነውም ብላለች፡፡
እንድ ቀን እኔም እንደ ሰው ወደ እንቅልፌ እንደምመለስ ተስፋ አደርጋለሁ የምትለው ትራን ቲ ሉ ባለቤቷ ላደረገላት ድጋፍ አመስግናለች፡፡
ይህች የእንቅልፍ ማጣት ህመምተኛ ቃለ መጠይቁን ከሰጠች በኋላ ጉዳዩ በመላው ቬትናም እና በእስያ መነጋገሪያ የሆነ ሲሆን ብዙዎቹ ነገሩ ተፈጽሟል ብለው እንደማያምኑ እና ትኩረት ለማግኘት የተደረገ ነው እያሉ እንደሆነ ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡