የህጻናቱ ወላጅ አባት መንታ እንተረገዘ ሲያውቅ መጥፋቱን እናትየው ተናግረዋል
ከ70 ዓመቷ ሚስቱ መንታ ልጆችን ያገኘው አባት መጥፋቱ ተገለጸ፡፡
በምስራቅ አፍሪካዊቷ ኡጋንዳ ያልተለመደ ነገር መከሰቱን ተከትሎ የሚዲያዎች ሁሉ ትኩረት ወደዛ ሆኗል፡፡
ሳፊና ናሙካዋያ የተባሉ የ70 ዓመት አዛውንት በኡጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ ነዋሪ ናቸው፡፡
ልጅ መውለድ መፈለጋቸውን ተከትሎ ለዓመታት ወደ ህክምና ተቋማት ክትትል ፍለጋ ሲመላለሱ ቆይተዋል፡፡
የካምፓላ ዓለም አቀፍ የጽንስ እና ሴቶች ሆስፒታል ደግሞ እኝህ አዛውንት የህክምና ድጋፍ ያደረጉበት ተቋም ነው፡፡
ኡጋንዳ "የሞቱ ምዕራባውያን" ልብስ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ እግድ ጣለች
በዚህ ሆስፒታል እርዳታ አማካኝነትም መንታ ልጆችን መውለድ እንደቻሉ የኡጋንዳው ኤንቲቪ ዘግቧል፡፡
እንደዘገባው ከሆነ እኝህ አዛውንት በ70 ዓመታቸው ባልተለመደ መልኩ አንድ ወንድ እና አንድ ሴት ህጻናትን ወልደው መታቀፍ ችለዋል፡፡
አሁን ላይ እናትም ሆነ ህጻናቱ በመልካም ጤንነት ላይ ናቸው የተባለ ሲሆን አባትየው ግን ጠፍቷል ተብሏል፡፡
"እየሱስን ለማግኘት" ወደ ኢትዮጵያ የመጡ 80 ኡጋንዳዊያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
እንደ እናትየው አስተያየት ከሆነ የህጻናቱ አባት የጠፋው መንታ ህጻናት እንደተረገዘ ከተነገረው ዕለት አንስቶ ነው፡፡
ሆስፒታሉ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ እንዳለው "የተፈጠረው ነገር የህክምና ስኬት አይደለም ፣ ክስተቱ የሰው ልጅ የስነ ልቦና ጥንካሬ እና አይበገሬነት መንፈስ ነው" ብሏል፡፡
የህጻናቱ እናት በበኩላቸው "ልጆች ስላገኘሁ በጣም ደስተኛ ነኝ ነገር ግን እንዴት አድርጌ እንደማሳድጋቸው አላውቅም" ብለዋል ተብሏል፡፡