"እየሱስን ለማግኘት" ወደ ኢትዮጵያ የመጡ 80 ኡጋንዳዊያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አማኞቹ ኢየሱስን ለመገናኘት ለ40 ቀናት እንዲጾሙም መደረጉ ተነግሯል
የኡጋንዳው ፓስተር ኦፖሎት ድርጊት አማኞችን እስከ ሞት እንዲጾሙ ካዘዙት ኬንያው ፓስተር ፖል ማኬንዚ ጋር ተመሳሳይነት አለው ተብሏል
ኢትዮጵያ ከኢየሱስ ጋር እንደሚገናኙ ቃል የተገባላቸውን 80 የኡጋንዳ አማኞች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ሁኔታ ማመቻቸቷ ተነግሯል።
አማኞችን አታለዋል የተባሉት ፓስተር ሲሞን ኦፖሎት በኡጋንዳ ምስራቃዊ ሶሮቲ ውስጥ ከሚገኘው የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ቤተ-ክርስቲያን ጋር ግንኙነት ያላቸው አማኞችን በማጭበርበር በደህንነት እየተፈለጉ ነው።
ኦፖሎት ተከታዮቻቸው ንብረታቸውን እንዲሸጡ እና ኢየሱስን ለመገናኘት እንዲዘጋጁ፤ ለዚህም በኢትዮጵያ ያሉት ብቻ እንደሚመረጡ መለኮታዊ ራዕይ ታይቶኛል በማለት አሳምነዋል ተብሏል።
- የዓለም ፍጻሜ ደርሷል በሚል ከኡጋንዳ ወደ ኢትዮጵያ መጡ ስለተባሉት ሰዎች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምን አለ?
- የዓለም ፍጻሜ ደርሷል በሚል ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ኡጋንዳዊያን ያንጋቶም እየኖሩ መሆኑ ተገለጸ
ምእመናኑ ንብረታቸውን ሸጠው ገንዘባቸውንም አደራ ሰጥተው በሞሮቶና በአሙዳት ወረዳዎች ተጉዘው ወደ ኢትዮጵያ ማቅናታቸው ታውቋል።
ቡድኑ በዚህ አመት ጥር እና መጋቢት መካከል ይህንን የነፍስ ጉዞ አድርገው ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል።
ኢትዮጵያ የኡጋንዳ ባለስልጣናትን በማነጋገር ዜጎቹ ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበትን አስፈላጊ ሰነዶች እና ዝግጅቶችን ማመቻቸቷ ተነግሯል።
የየኡጋንዳ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ሲሞን ፒተር ሙንዴይ ፓስተር ኦፖሎት ኢየሱስን በ41ኛው ቀን ለመገናኘት ለ40 ቀናት እንዲጾሙም አሳምኗቸዋል ብለዋል።
ኦፖሎት ለኢትዮጵያ መለኮታዊ ግንኙነት ዓለም በፍጥነት ይጠፋል ብለው ለተከታዮቻቸው ተናግረዋል ተብሏል።
ተከታዮቹ መምህራንና የመንግስት ሰራተኞችን ጨምሮ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ የተማሩ ግለሰቦች መሆናቸውንም ታውቋል።
ስደተኞቹ በአድካሚ ጉዞ እና የእለት ምግብ እጥረት ምክንያት ከፍተኛ የአካል ጉዳታቸው መጋለጣቸውን የኡጋንዳ ባለስልጣናት ገልጸዋል።
ደህንነታቸውን በማረጋገጥ ረገድ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጣልቃ ገብነት ወሳኝ ሚና መጫወቱንም እንዲሁ።
የኦፖሎት ድርጊት ከኬንያው ፓስተር ፖል ማኬንዚ ጋር ተመሳሳይነት አለው ተብሏል።
የኬንያው ፓስተርም ተከታዮቻቸውን ወደ መንግስተ ሰማይ ለመሄድ እስከ ሞት ድረስ እንዲጾሙ አድርገዋል።