አዳማ ባሮው ለሁለተኛ ጊዜ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ አሸነፉ
ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ጋምቢያ በትናንትናው ዕለት ፕሬዘዳናታዊ ምርጫ አካሂደዋል፡፡
በዚህ ምርጫ ላይ ላለፉት አምስት ዓመታት ጋምቢያን በፕሬዘዳናትነት የመሩት አዳማ ባሮው 53 በመቶ የመራጮችን ድምጽ በማግኘት ማሸነፋቸውን ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል፡፡
በፕሬዘዳናታዊ ምርጫው ላይ ብርቱ ተፎካካሪ የነበሩት ኦሴኑ ዳርቤ በአዳማ ባሮው ተሸንፈዋል፡፡
አዳማ ባሮው በፈረንጆቹ 2016 ዓመት በተካሄደው ፈታኝ ምርጫ ሀገሪቱን ከ20 ዓመት በላይ በፕሬዘዳንትነት የመሩት ያሕያ ጃሜን በመርታት ፕሬዘዳንት ሆነው መመረጣቸው ይታወሳል፡፡
ለሁለተኛ ጊዜ ፕሬዘዳንት ሆነው የተመረጡት አዳማ ባሮው ግብርናን መሰረተ ልማትን ማዘመን በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ትኩረት የሚሰጡባቸው ጉዳዮች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በምእራብ አፍሪካ በቆዳ ስፋት ትንሿ አገር የሆነችው ጋምቢያ 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ህዝብ ብዛት ያላት ሲሆን ግብርና እና ቱሪዝም ዋነኛ የገቢ ምንጮች ናቸው፡፡