የዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛ ተመራማሪ ዶ/ር ሶዩምያ ሻሚናታን ዓለም በ‘ኦሚክሮን’ መደናገጥ የለበትም” አሉ
ዶ/ር ሶዩምያ ሻሚናታን ዝርያው በከፍተኛ ሁኔታ ከሰው ወደ ሰው የሚተለለፍ በመሆኑ ጥንቃቄ አስፈላጊ ነውም ብሏል
ኦሚክሮን መገኘቱን ተከትሎ አሜሪካን ጨምሮ በርካታ ሀገራት በደቡብ አፍሪካ ላይ የበረራ እገዳ መጣላቸው ይታወቃል
በአዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ “ኦሚክሮን” ምክንያት ዓለም መደናገጥ እንደሌለበት የዓለም ጤና ድርጅት አሳሰበ፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛ ተመራማሪ ዶ/ር ሶዩምያ ሻሚናታን አርብ እለት አንድ ኮንፍረንስ ላይ ባደረጉት ንግግር “ጥንቃቄ ማድረግ ነው እንጂ፤ መፍራት አያስፈልግም” ሲሉ ተደምጧል፡፡
አሁን ዓለም ያለችበት ሁኔታ አምና ከነበረው የተለየ ነው ያሉት ተመራማሪዋ ፤ ዓለም ጭንቀት ውስጥ ከመግባት ይልቅ ጥንቃቄ ላይ ማተኮር እለበት ሲሉ መናገራቸውም ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
"ለመገመት ከባድ ቢሆንም ዝርያው በዓለም የሚሰራጭ ሊሆን ይችላል፤ለምሳሌ ዴልታ ዝርያ በዓለም ካሉ በበሽታው ከተያዙ ሰዎች 99 በመቶ ይሸፍናል" ሲሉም አክለዋል።
ዶ/ር ሶዩምያ በደቡብ አፍሪካ የተሠራ ጥናትን አጣቅሰው "ዝርያው በከፍተኛ ሁኔታ ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል"ም ብለዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት የድንገተኛ ጊዜ ኃላፊ ማይክ ራየን በበኩላቸው ፤አሁን ትኩረት መሰጠት ያለበት የኮሮናቫይረስ ክትባትን ማዳረስ ላይ እንደሆነ ተናግረዋል።ኦሚክሮን መገኘቱን ተከትሎ ሀገራት በደቡብ አፍሪካ ላይ የበረራ እገዳ ጥለዋል።
በአሜሪካ የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ሰዎች ላይም አዲሱ ዝርያ መገኘቱን ተከትሎ፤ወደ ግዛቷ የሚገቡ ተጓዦች ከበረራቸው አንድ ቀን አስቀድሞ የኮቪድ-19 ምርመራ እንዲያደርጉ መመሪያ ሰጥታለች።
ጀርመን ያልተከተቡ ዜጎቿን ከመደብር፣ መዝናኛ እና ፊልም ቤት ስታግድ ኦስትሪያ ደግሞ ክትባት መውሰድ ግዴታ ነው የሚል መመሪያ አውጥታለች።
ህንድም የ66 ዓመት ደቡብ አፍሪካዊ እና የ46 ዓመት ህንዳዊ ሐኪም ላይ ዝርያውን ማግኘቷን አስታውቃለች።
ዩናይትድ ኪንግደም በበኩሏ 114 ሚሊዮን የፋይዘር እና ሞደርና ክትባቶች ገዝታለች። ጎልማሶች የኮሮናቫይረስ ክትባት ማጠናከሪያ (ቡስተር) ክትባት እንዲወስዱም እየገፋፋች ነው።
የአውሮፓ ሀገራት የወረርሽኙን ዳግመኛ ስርጭት ለመቆጣጠር እየሞከሩ ባለበት ወቅት ነው አዲሱ ዝርያ የተከሰተው።
ኦሚክሮን እስካሁን ድረስ በ40 ሀገራት የተገኘ ሲሆን ፤ዝርያው በክትባት አማካይነት የሚገታ መሆኑንና አለመሆኑን በተመለከተ እስካሁን ግልጽ የሆነ ነገር የለም፡፡