ልዩልዩ
ሳትታገት ታግቻለው ብላ የፍቅር ጓደኛዋን 500 ሺህ ብር የጠየቀችው ግለሰብ በፖሊስ ተያዘች
ታግቻለሁ ያለችው ይህች በመኖሪያ ቤቷ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሏ ተገልጿል
ተጠርጣሪዋ ግለሰብ የማታለል ወንጀሉን የፈፀመችው በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ጎሮ አይሲቲ አካባቢ ነው ተብሏል
ሳትታገት ታግቻለው ብላ የፍቅር ጓደኛዋን 500 ሺህ ብር የጠየቀችው ግለሰብ በፖሊስ ተያዘች።
የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዳስታወቀው ግለሰቧ ለቦታ መያዣ ተብለው ከተሰሩ የጎጆ ዳስ ውስጥ ታግቻለሁ በማለት የፍቅር ጓደኛዋን 500 ሺህ ብር እሱ በማያውቀው ስልክ መክፈል አለብሽ ተብያለሁ በማለት መልዕክት ስትልክለት እንደነበር ገልጿል።
የግል ተበዳይ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ መሰረትም ግለሰቧ መያዟን እና የላከችው መልዕክት ሃሰት መሆኑን መረጋገጡን የለሚኩራ ክፍለከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መርማሪ ሣጅን እንግዳ በላይ ተናግረዋል።
ተከሳሽና የግል ተበዳይ ከዚህ ቀደም በትዳር አብረው እየኖሩ የነበሩና ተጣልተው መለያየታቸውን የገለፁት መርማሪው ታርቀው እሷ ተከራይታ እንደምትኖር የጠቆሙት መርማሪው የውሸት መልዕክቶችን አጋቾች እንደፃፉት አስመስላ ስትፅፍ እንደነበርም ተገልጿል።
ህብረተሰቡ መሰል የወንጀል ተግባር ሰለባ ላለመሆን ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርግ እና ምንም ጉዳይ ቢሆን ገንዘቡን ፈጥኖ ከመስጠት እንዲቆጠብ እና ጥቆማ እንዲሰጥም ፖሊስ አሳስቧል።