ልዩልዩ
“ጉዳዬ ምላሽ አላገኘም” ያሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባል የወረዳ አመራርን ገደሉ
ግድያውን ፈጽመዋል በሚል የተጠረጠሩት የፖሊስ አባሉ በቁጥጥር ስር ውለዋል
ተጠርጣሪው "ጉዳዬ ምላሽ አላገኘም" በሚል በታጠቁት መሳሪያ ስራ አስፈጻሚውን መግደላቸውን ፖሊስ አስታውቋል
በአዲስ አበባ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት ስራ አስፈፃሚ በፖሊስ ተገደሉ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ዋና ስራ አስፈጻሚ አለባቸው አሞኜ ዛሬ ጠዋት በቢሯቸው ተገድለዋል።
ስራ አስፈጻሚው "የህዝብ አገልግሎት" ሲሰጡ ተገልጋይ ነበሩ በተባሉ የፖሊስ ባልደረባ በጥይት ተመተው ህይወታቸው ማለፉን የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ ገልጿል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ግድያውን የካዛንቺስ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አባል መፈጸሙን አስታውቋል።
የፖሊስ አባሉ 'ጉዳዬ ምላሽ አላገኘም' በሚል እርምጃውን እንደወሰዱ ተነግሯል።
"ፖሊሱ ጉዳዬ እንዳይፈጸም የከለከልከው አንተ ነህ በሚል ምክንያት የወረዳውን ዋና ስራ አስፈጻሚ ቢሯቸው ውስጥ በስራ ላይ እንዳሉ በታጠቀው ሽጉጥ መግደሉ ታውቋል" ብሏል፡፡
ወንጀሉን የፈጸመው የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው እየተደረገባቸው እንደሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።