በቂ ፋይናንስ ማሰባሰብ የአየር ንብረት ለውጥ ግቦችን ለማሳካት ወሳኝ ነው- ማህሙድ ሞሂልዲን
ሞህልዲን ይህን የተናገሩት በሞሮኮ በተደረገው የአየር ንብረት እና የደህንነት ስብሰባ ላይ ነው
የተመድ የ2030 ዘላቂ ልማት ፋይናንሲንግ ልዩ መልክተኛ የሆኑት ሞሂልዲን የአየረ ንብረት ለውጥ በዓለም ደረጃ አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን አረጋግጠዋል
በቂ እና ፍትሃዊ የሆነ ፋይናንስሮረ የአየር ንብረት ለውጥ ግቦችን ለማሳካት ወሳኝ መሆኑን ግብጻዊው ዶክተር ማህመድ ሞሂልዲን ተናገሩ።
የተመድ የ2030 ዘላቂ ልማት ፋይናንሲንግ ልዩ መልክተኛ የሆኑት ሞሂልዲን የአየረ ንብረት ለውጥ በዓለም ደረጃ አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን አረጋግጠዋል።
ይህ የሆነው መካከለኛው ምስራቅን እና የተወሰኑ የአፍሪካ ቀጣናዎችን ጨምሮ በተከሰተው የሙቀት መጠን መጨመር ምክንያት መሆኑን ሞሂልዲን ይናገራሉ።
ሞህልዲን ይህን የተናገሩት በሞሮኮ በተደረገው የአየር ንብረት እና የደህንነት ስብሰባ ላይ ነው።
ሞሂልዲን አለምአቀፍ የሆኑ ሪፖርቶችን ጠቅሰው እንደተናገሩት ከ2021-22 አማካኝ የአየር ንብረት ፋይናንሲንግ 1.27 ትሪሊየን ዶላር ደርሷል። ሞሂልዲን እንዳሉት ከተሰበሰበው ገንዘብ ውስጥ 91 በመቶ የሚሆነው የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ችግር ለመቀነስ የዋለ ሲሆን አምስት በመቶ የሚሆነው ብቻ ብክለትን ለመከላከል መዋሉን ገልጸዋል።