ኢኮኖሚ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አራት ከተሞች አዲስ በረራ ሊጀምር መሆኑን ገለጸ
አየር መንገዱ ዓለም አቀፍ የመዳረሻ ቦታዎቹን ወደ 271 የማድረስ እቅድ እንዳለው ገልጿል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቀናት በፊት 78 አዲስ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ስምምነት መፈራረሙ ይታወሳል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አራት ከተሞች አዲስ በረራ ሊጀምር መሆኑን ገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተያዘው ዓመት አዲስ እና ነባር በረራ ስፍራወዎችን እንደሚጨምር የገለጸ ሲሆን ማድሪድ፣ፍሪታወን፣ሀኖይ እና አምስተርዳም ዋነኛዎቹ እንደሆኑ አስታውቋል፡፡
አየር መንገዱ ባሳለፍነው ሳምንት በዱባይ በተካሄደ ዓለም አቀፍ የአቪዬሽን አውደ ርዕይ ላይ ከቦይንድ 67 እንዲሁም 11 ከኤርባስ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ስምምነት መፈጸሙ ይታወሳል፡፡
አሁን ላይ 136 ዓለም አቀፍ የመዳረሻ ብዛት ያለው አየር መንገዱ በ2035 ላይ የመዳረሻ ከተሞቹን ወደ 271 የማድረስ ግብ እንዳለውም አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባሳለፍነው ዓመት 13 ነጥብ 7 ሚሊዮን መንገደኞችን እንዳጓጓዘ የገለጸ ሲሆን ትርም 6 ቢሊዮን ዶላር እንደነበር መግለጹ አይዘነጋም፡፡