በደቡብ አፍሪካ ተቀባይነት ያጣችው አዴሽና በናይጀሪያ የቁንጅና ውድድር አሸነፈች
አደሽና በሚቀጥለው ህዳር በሜክሲኮ በሚካሄደው አለምአቀፍ የቁንጅና ውድድር ላይ ናይጄሪያን ወክላ ትሳተፋለች
ባለፈው ወር በደቡብ አፍሪካ በተካሄደ የቁንጅና ውድድር አወዛጋቢ የነበረችው አዴሽና በናይጀሪያ ቆይጆ ተብላ ዘውድ ደፍታለች።
በደቡብ አፍሪካ ተቀባይነት ያጣችው አደሽና በናይጀሪያ የቁንጅና ውድድር አሸነፈች።
ባለፈው ወር በደቡብ አፍሪካ በተካሄደ የቁንጅና ውድድር አወዛጋቢ የነበረችው ቺድንማ አዴሽና በናይጀሪያ ቆንጆ ተብላ ዘውድ ደፍታለች።
ከናይጀሪያዊ አባት እና ከደቡብ አፍሪካዊት እናቷ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የተወለደችው እና የደቡብ አፍሪካ ዜግነት ያላት የ23 አመቷ አዴሽና፣ በሀገሪቱ መነጋገር የሆነችው ሚኒስትሮችን ጨምሮ ጥቂት ደቡብ አፍሪካውያን በዘር ግንዷ ምክንያት በተሳትፎዋ ላይ ጥያቄ ካነሱ በኋላ ነው።
ይህን ተከትሎም አደሽና ከውድድሩ ራሷን ማግለሏ ይታወሳል።
"ይህ ዘውድ የቁንጅና ብቻ ሳይሆን እንድ የሚያደርገንም መሆኑን ሁለም ሰው እንዲያውቅ እፈልጋለሁ። በሚስ ዩኒቨርስ ውድድር ናይጀሪያን በመወከሌ ኩራት ይሰማኛል፤ ማሸነፋችንም አይቀሬ ነው" ሰትል አዴሽና በደስታ ሰሜት ውስጥ ሆና ለታማዳሚዎች ተናግራለች።
በአዴሽና ዙሪያ የተነሳው ውዝግብ በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ናይጀሪያውያን ነጋዴዎች ላይ ሲደርስ የነበረው ጥቃት አንዲታወስ አድርጎታል።
አዴሽና በሚቀጥለው ህዳር በሜክሲኮ በሚካሄደው አለምአቀፍ የቁንጅና ውድድር (ሚስ ዩኒቨርስ) ላይ ናይጄሪያን ወክላ ትሳተፋለች።
በደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ዜጎች "የመጤ ጠል" ወይም የዜኖፎቢክ ጥቃት ሰላባ ሲሆኑ ቆንተዋል።በጥቃቱ በርካታ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን የንብረት ውድመትም ደርሷል።