ከፋፋይ ዘመቻዎች በታዩበት የቁንጅና ውድድር መስማት የተሳናት ደቡብ አፍሪካዊት አሸነፈች
ባለፈው ሳምንት የህግ ተማሪ የሆነችው ችዲማ አደሺና እኗታ የደቡብ አፍሪካ ሴት ማንነት ሰርቃለች የሚል አሉባልታ መወራቱን ተከትሎ ከውድድሩ ወጥታለች
ሊ ሮክስ ባደረገችው ንግግር ማሸነፏ በማህበረሰቡ የተገለሉ "ህልማቸውን እንደ እኔ" እንዲያሳኩ ይረዳቸዋል ብላ ተስፋ እንደምታደርግ ተናግራለች
የመጀሪያዋ መስማት የተሳናት ደቡብ አፍሪካዊ የቁንጅና ውድድር አሸነፈች።
ሚያ ሊ ሮክስ የተባለችው መስማት የተሳናት ደቡብ አፍሪካዊ፣ አንድ የናይጀሪያ ዝርያ ያላት የመጨረሻ ተወዳዳሪ ራሷን ባገለለችበት ከፋፋይ ውድድር የደቡብ አፍሪካ ቆንጆ ተብላ ዘውድ መድፋቷን ቢቢሲ ዘግቧል።
ሊ ሮክስ ባደረገችው ንግግር ማሸነፏ በማህበረሰቡ የተገለሉ "ህልማቸውን እንደ እኔ" እንዲያሳኩ ይረዳቸዋል ብላ ተስፋ እንደምታደርግ ተናግራለች።"በፋይናንስ የተገለሉ ወይም የአካል ጉዳት" ያለባቸውን ሰዎች የመርዳት ፍላጎት እንዳላት ገልጻለች።
ባለፈው ሳምንት የህግ ተማሪ የሆነችው ችዲማ አደሺና እኗታ የደቡብ አፍሪካ ሴት ማንነት ሰርቃለች የሚል አሉባልታ መወራቱን ተከትሎ ከውድድሩ ወጥታለች።አደሺና ከናይጀሪያዊ አባት እና የሞዛምቢካዊ ዝርያ ካላት እናቷ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ነው የተወለደችው። ሚኒስትሮችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ደቡብ አፍሪካን መወከል አትችልሞ በሚል በማህበራዊ ሚዲያ ለበርካታ ሳምንታት ዘመቻ ሲያካሄዱባት ቆይተዋል።
አደሺና "ጥቁር በጥቁር ላይ በሚያርገው ጥላቻ" ወይም ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የመጡ ዜጎችን ኢላማ ባደረገው ጥላቻ (አፍሮፎቢያ) ሰለባ እንደሆነች ተናግራለች።
የ28 አመቷ ሊ ሮክስ በአንድ አመቷ ነበር የመስማት ችግር ያጋጠማት። ሊ ሮክስ እንደገለጸችው የመጀመሪ ቃል ከማውጣቷ በፊት የአንድ አመት የቆየ የንግግር ልምምድ አድርጋለች።
ሞዴሏ እና የማርኬቲንግ ስራ አስኪያጅ የሆነችው ሊ ሮክስ ካሸነፈች በኋላ "ኩሩ ደቡብ አፍሪካዊ መስማት የተሳነኝ ሴት ነኝ፤ መገለል የሚፈጥረውን ስምትም አውቃለሁ" ስትል ተናግራለች።
"የማይቻሉ ነገሮችን ለማድረግ ወደ እዚህ ምድር እንደመጣሁ አውቃለሁ፣ ዛሬ ምሽት አሳክቸዋለሁ"ብላለች።
ከፋፋይ ዘመቻ በታዩበት የቁንጅና ውድድር መስማት የተሳናት ደቡብ አፍሪካዊት አሸነፈች