የውድድሩ አስተናጋጅ ሀገር ኮቲዲቯር ከሴኔጋል የሚያደርጉት ትንቅንቅም ይጠበቃል
በኮቲዲቯር እየተካሄደ የሚገኘው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች ትናንት ማምሻውን ተጠናቀው ጥሎ ማለፉን የተቀላቀሉ 16 ሀገራት ተለይተዋል።
ከስድስቱ ምድብ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃን የያዙ 12 ሀገራት እና አራት ምርጥ ሶስተኛ ብሄራዊ ቡድኖች ጥሎ ማለፉን መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል።
በምድብ ጨዋታ በኢኳቶሪያል ጊኒ የ4 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዳ ከውድድሩ ለመሰናበት ጫፍ ላይ የነበረችው አስተናጋጇ ሀገር ኮትዲቯር ምርጥ ሶስተኛ ሆና ጥሎ ማለፉን ተቀላቅላለች።
የአምስት ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮኗ ጋና፣ በ1990 ራሷ ያዘጋጀችውን፤ በ2019 ደግሞ ግብጽ ያስተናገደችውን የአፍሪካ ዋንጫ ያነሳችው አልጀሪያ እና የ2004 ሻምፒዮኗ ቱኒዚያ ከኮቲዲቯሩ የአፍሪካ ዋንጫ ተሰናብተዋል።
የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ቅዳሜ ሲጀመሩ ናይጀሪያ ከካሜሮን፤ አንጎላ ከናሚቢያ ይጫወታሉ።
እሁድ ደግሞ ግብጽ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፤ ኢኳቶሪያል ጊኒ ከጊኒ ሩብ ፍጻሜውን ለመቀላቀል ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ሰኞ ምሽት 2 ስአት የውድድሩ አስተናጋጅ ሀገር ኮቲዲቯር ከሴኔጋል የሚያደርጉት ትንቅንቅ ይጠበቃል። ከዚህ ጨዋታ ቀደም ብሎ ኬፕ ብቨርዴ ከሞሪታንያ ይጫወታሉ።
በጥሎ ማለፉ ማሊ ከቡርኪናፋሶ፤ ሞሮኮ ከደቡብ አፍሪካ ይፋለማሉ።
ከየምድቡ ወደ 16ቱ መግባት የቻሉ ብሄራዊ ቡድኖችን ዝርዝር ይመልከቱ፦