የአፍሪካ ዋንጫን ያነሱ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
አባይ ባስተሳሰራቸው ሶስት ሀገራት በተጀመረው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ በ1962 ግብጽን አሸንፋ ዋንጫውን መውሰዷ ይታወሳል
14 የተለያዩ ሀገራት የአፍሪካ ዋንጫን ማንሳት ችለዋል
በፈረንጆቹ 1957 በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ የተጀመረው የአፍሪካ ዋንጫ አሁን ግዙፉ አህጉራዊ የእግርኳስ መድረክ ሆኗል።
ውድድሩ በ1968 የተሳታፊዎቹን ቁጥር ወደ ስምንት አሳድጓል፤ በ1992 ወደ 12 በ1996 ደግሞ ወደ 16 ከፍ ማድረጉ ይታወሳል።
የአፍሪካ ዋንጫ መልክና ቅርጽን በማስያዝ ኢትዮጵያዊው ይድነቃቸው ተሰማ በታሪክ ሲወሳ የሚኖር ትልቅ ሚና ተጫውተዋል።
የመጀመሪያውን የአፍሪካ ዋንጫ (1957) ያነሳችው ግብጽ ናት፤ በፍጻሜው ኢትዮጵያን 4 ለ 0 በመርታት።
ኢትዮጵያም በአዲስ አበባ ያዘጋጀችውን ሶስተኛ የአፍሪካ ዋንጫ ግብጽን በፍጻሜው በማሸነፍ የመጀመሪያውን እና ሊደገም ያልቻለውን ዋንጫ ማንሳቷ ይታወሳል።
ሌላኛዋ የአፍሪካ ዋንጫ መስራች ሀገር ሱዳንም ከ1970ው ድል በኋላ ዋንጫውን ወደ ካርቱም መመለስ አልቻለችም።
በአንጻሩ በአፍሪካ ዋንጫው ምስረታ ዋንጫውን በማንሳት አሃዱ ያሉት ፈርኦኖቹ ሰባት ጊዜ ዋንጫዎችን በማንሳት የሚስተካከላቸው አልተገኘም።
የማዕከላዊ አፍሪካዊቷ ሀገር ካሜሮን ደግሞ አምስት ጊዜ ዋንጫውን በመውሰድ ትከተላለች።
በ33 የአፍሪካ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታዎች 14 የተለያዩ ሀገራት ሻምፒዮን ሆነው ዋንጫ ማንሳት ችለዋል።
በአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮን የሆኑ ሀገራትና የፍጻሜ ተፋላሚዎቻቸውን ዝርዝር ይመልከቱ፦