በአፍሪካ ዋንጫው ጥሎ ማለፉን የተቀላቀሉት 16 ሀገራት እነማን ናቸው?
አሰልጣኟን ያሰናበተችው የውድድሩ አስተናጋጅ ኮቲዲቯር ምርጥ ሶስተኛ ሆና ጥሎ ማለፉን ተቀላቅላለች
የአራት ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮና ጋና፣ ቱኒዚያ እና አልጀሪያ ከውድድሩ ተሰናብተዋል
በኮቲዲቯር እየተካሄደ የሚገኘው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች ትናንት ማምሻውን ተጠናቀዋል።
በውድድሩ ጥሎ ማለፉን የተቀላቀሉ 16 ሀገራትም ተለይተዋል፤ ከስድስቱ ምድብ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃን የያዙ 12 ሀገራት እና አራት ምርጥ ሶስተኛ ብሄራዊ ቡድኖች ጥሎ ማለፉን ተቀላቅለዋል።
በምድብ ጨዋታ በኢኳቶሪያል ጊኒ የ4 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዳ ከውድድሩ ለመሰናበት ጫፍ ላይ የነበረችው አስተናጋጇ ሀገር ኮትዲቯር ምርጥ ሶስተኛ ሆና ጥሎ ማለፉን ተቀላቅላለች።
የሰባት ጊዜ ሻምፒዮኗ ግብጽ ሶስቱንም የምድብ ጨዋታዎች በተመሳሳይ 2 ለ 2 ብታጠናቅቅም ከምድቧ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ 16ቱ ውስጥ ገብታለች።
በኬፕቨርዴ ተሸንፋ ከግብጽና ሞዛምቢክ ነጥብ የተጋራችውና የአፍሪካ ዋንጫውን አምስት ጊዜ ያነሳችው ጋና ከውድድሩ ተሰናብታለች።
ከምድብ ሶስት ሴኔጋል በ9 ነጥብ ካሜሮን እና ጊኒ ደግሞ በተመሳሳይ 4 ነጥብ ጥሎ ማለፉን መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል።
በ1990 ራሷ ያዘጋጀችውን፤ በ2019 ደግሞ ግብጽ ያስተናገደችውን የአፍሪካ ዋንጫ ያነሳችው አልጀሪያ እና የ2004 ሻምፒዮኗ ቱኒዚያ ከኮቲዲቯሩ የአፍሪካ ዋንጫ ተሰናብተዋል።
ከየምድቡ ማለፋቸውን ያረጋገጡ ሀገራትን ዝርዝር ይመልከቱ፦
ምድብ 1
1. ኢኳቶሪያል ጊኒ
2. ናይጀሪያ
3. ኮቲዲቯር (ምርጥ ሶስተኛ)
ምድብ 2
1. ኬፕ ቨርዴ
2. ግብጽ
ምድብ 3
1. ሴኔጋል
2. ካሜሮን
3. ጊኒ (ምርጥ ሶስተኛ)
ምድብ 4
1. አንጎላ
2. ቡርኪናፋሶ
3. ሞሪታንያ
ምድብ 5
1. ማሊ
2. ደቡብ አፍሪካ
3. ናሚቢያ
ምድብ 6
1. ሞሮኮ
2. ዲአር ኮንጎ