በአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ 5 ቡድኖች ወደ መጨረሻ 16ቱ ውስጥ ማለፋቸውን አረጋገጡ
ሁሉም ቡድኖች እስካሁን ቢያንስ ሁለት ጊዜ መጫወት የቻሉ ሲሆን የተወሰኑ ቡድኖች ናቸው ወደ ቀጣይ ዙር ያለፉት
አስተናጋጇ አይቮሪኮስት በኢኳቶሪያል ጊኒ 4-0 በሆነ ሰፊ ውጤት ከተሸነፈች በኋላ ከምድቡ ወደ ቀጣይ ዙር ከሚያልፉት ሁለት ቡድኖች ውጭ ሆናለች
በአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ የ5 ሀገራት ብሔራዊ ቡድኖች ወደ መጨረሻ 16ቱ ውስጥ ማለፋቸውን አረጋገጡ።
በኮትዲቮረ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ጨዋታ እስካሁን አምስት ብሔራዊ ቡድኖች ወደ መጨረሻዎቹ 16ቱ ውስጥ ማለፍ ችለዋል።
ሁሉም ቡድኖች እስካሁን ቢያንስ ሁለት ጊዜ መጫወት የቻሉ ሲሆን የተወሰኑ ቡድኖች ናቸው ወደ ቀጣይ ዙር ያለፉት።
ይህ በርካታ ጨዋታዎች እንደሚቀሩ ያሳያል።
አስተናጋጇ አይቮሪኮስት በኢኳቶሪያል ጊኒ 4-0 በሆነ ሰፊ ውጤት ከተሸነፈች በኋላ ከምድቡ ወደ ቀጣይ ዙር ከሚያልፉት ሁለት ቡድኖች ውጭ ሆናለች።
በስድስቱ ቡድኖች ከተደለደሉት ውስጥ ሁለት ምረጥ ቡድኖች እና አራት ምርጥ ሶስተኛ ሆነው የጨረሱ ቡድኖች የመጨረሻዎቹ 16 ቡድኖች እንደሚሆኑ ዩሮ ስፖርት ዘግቧል።
በርካታ ትላልቅ ስም ያላቸው ቡድኖች ወደዚህ ዙር የመካተት እድላቸውን ሊያጡ ይችላሉ።
እስካሁን በተካሄዱ ጨዋታዎች ኢኳቶሪያል ጊኒ እና ናይጀሪያ ከምድብ አንድ፣ ኬፕቨርዴ እና ግብጽ ከምድብ ሁለት እንዲሁም ሴኔጋል ከምድብ ሶስት ወደ ቀጣይ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።
እስካሁን ከውድድሩ መውጣታቸውን ያረጋገጡት ሁለት ቡድኖች ደግሞ ጊኒቢሳው ኤና ሞዛምፒክ ናቸው።
ጨዋታዎች በዛሬው እለትም ቀጥለው ይካሄዳል።
በዛሬው ምሽት 2 ሰአት ላይ ጋምቢያ ከካሜሩን፣ ጊኒ ከሴኔጋል የሚጫወቱ ሲሁን ምሽት 5 ሰአት ደግሞ ማውርታኒያ ከአልጀሪያ እንደሚጫወቱ መርሀግብሩ ያመለክታል።