የአፍሪካ ዋንጫ ሻፒዮኗ ሴኔጋል ከካሜሮን የሚያደርጉት ጨዋታ ዛሬ ይጠበቃል
34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ባሳለፍነው ቅዳሜ መካሄድ የጀመረ ሲሆን፤ 7ኛ ቀኑን አስቆጥሯል።
ጨዋታው በትናንትናው በ2ኛ ዙር የምድብ ጨዋታዎች እለት ቀጥሎ የተካሄደ ሲሆን፤ በምድብ 1 አይቮሪኮስት ከናይጄሪያ እንዲሁም ኪኒ ቢሳው ከኢኳቶሪያል ጊኒ ጨዋታቸውን አድርገዋል።
የሞት ምድብ በተባለው ምድብ ሁለት የተደለደሉት ግብጽ እና ጋናም በትናትናው እለት ተጠባቂውን ጨዋታቸውን አድርገዋል።
በምድብ አንድ የዘንድሮ የአፍሪካ ዋንጫ አስተናጋጇ አይቮሪኮስትን ከናይጄሪያ ጋር ያገናኘው ጨዋታ በናይጄሪያ 1ለ0 አሸናፊነት የተጠናቀቀ ሲሆን፤ የናይጄሪያን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ዊሊያም ተሩስት በ55ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል።
በዚሁ ምድብ በተደረገ ሌላ ጨዋታ የኢኳቶሪያ ጊኒ ብሄራዊ ቡድን የጊኒ ቢሳው አቻውን 4ለ2 በሆነ ውጤት መሸነፍ ችሏል።
በጨዋተው ላይ 34 ዓመቱ የኢኳቶሪያል ጊኒ ተጫዋች ኢሚሊዮ ኒሱን 3 ግቦች በማስቆጠር ሀትሪክ መስራት ችሏል።
በእስካሁን ጨዋታ ኢኳቶሪያል ጊኒ 4 ነጠብ በመሰብሰብ ምድቧን በመምራ ላይ ትገኛለች።
ሌላኛው የትናንት ተጠባቂ ጨዋታ የነበረው የሞት ምድብ በተባለው ምድብ ሁለት የተደለደሉትን ጋናን ከግብጽ ያፈገናኘው ጨዋታ ሲሆን፤ ጨዋታውም 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።
የጋናን ሁለት ግቦች ሞሀመድ ኩዱስ ከመረብ ሲያሳርፍ የግብፅን የአቻነት ግቦች ሙስጠፋ ሞሀመድ እና ማራሙሽ አስቆጥረዋል።
ጨዋታው በዛሬው እለትም ቀጥሎ የሚካሄድ ሲሆን፤ በምድብ 2 ቀሪ ጨዋታ ኬፕቨርዱ ከሞዛሚቢክ ጨዋታቸውን 11 ሰዓት ላይ ያደርጋሉ።
በምድብ ሶስት ጨዋታ የአፍሪካ ዋንጫ ሻፒዮኗ ሴኔጋል ከካሜሮን የሚያደርጉት ጨዋታ ዛሬ ምሽት 2 ሰዓት ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
በዚ ምድብ የጠደለደሉት ጋሚያ እና ጊኒም ጨዋታቸውን ምሽት 5 ሰዓት ላይ ያደርጋሉ።