የአፍሪካ ልማት ባንክ በኢትዮጵያ አቋርጦት የነበረውን ስራ እንደሚጀምር ተገለጸ
ባንኩ በጠፋው ገንዘብ ጉዳይ ለሚደረግ ምርመራ ለመተባበር መንግስት ቁርጠኛ ሆኗል ብሏል
የአፍሪካ ልማት ባንክስራውን በድጋሚ የሚጀምረው መንግሰት ለሰራተኞቹ የደህንነት ዋስትና ስለተሰጠው እና ይፋዊ ይቅርታ ስለጠየቀው ነው ተብሏል
የአፍሪካ ልማት ባንክ በኢትዮጵያ አቋርጦነት የነበረውን ስራ እንደሚጀምር ተገለጸ።
የአፍሪካ ልማት ባንክ(ኤኤፍዲቢ) ስራውን በድጋሚ የሚጀምረው መንግሰት ለሰራተኞቹ የደህንነት ዋስትና ስለሰጠው እና ይፋዊ ይቅርታ ስለጠየቀው ነው ተብሏል።
- የአፍሪካ ልማት ባንክ በኢትዮጵያ ያሉ ሰራተኞቹ ድብደባና እስር እንደተፈጸመባቸው ገለጸ
- የአፍሪካ ልማት ባንክ በኢትዮጵያ ያሉ ሰራተኞቹ ድብደባና እስር እንደተፈጸመባቸው ገለጸ
ባንኩ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በሰራተኞቹ ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ተከትሎ ያስወጣቸውን ሁሉንም አለምአቀፍ ሰራተኞች በኋላ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመልስ ማስታወቁን ሮይተርስ ዘግቧል።
ባንኩ የኢትዮጵያ መንግስት በሰራተኞቹ ላይ የደረሰውን ጥቃት በሚገባ መርምሮ ውጤቱን እንዳላሳወቀው እና ለሰራተኞቹ ደህንነት ዋስትና አለመኖሩን በመጥቀስ ነበር ከወር በፊት አለምአቀፍ ሰራተኞቹን ያስወጣው።
ባንኩ ባወጣው መግለጫ እንደገለጸው ከባለስልጣናት የደህንነት ዋስትና ካገኘ በኋላ መደበኛ አገልግሎቱን ይጀምራል።
ባለፈው ወር በባንኩ ፕሬዝደንት አኪንውሚ አደሲና እና በጠቅላይ ማኒስትር ዐቢይ አህመድ መካከል በተካሄደው ውይይት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ባንኩን ይቅርታ መጠየቃቸውን እና ለባንኩ ሰራተኞች የደህንነት ዋስተና መስጠታቸውን መግለጫው ጠቅሷል።
መግለጫው አክሎም ለባንኩ ሊተላለፍ በነበረው እና በጠፋው ገንዘብ ጉዳይ ለሚደረግ ምርመራ ለመተባበር መንግስት ቁርጠኛ ሆኗል ብሏል።
ባንኩ በይፋ በሰራተኞቹ ላይ ስለደሰው ጥቃት በይፋ ሲናገር የመጀመሪያው ነው።
የኢትዮጵያ መንግስት በዚህ ጉዳይ ምንም አስተያየት አልሰጠም።
ባንኩ በመግለጫው "በአደሲና እና በዐቢይ መካከል የተካሄደውን ውጤታማ ወይይት ከግምት ውስጥ በማስገባት እና መንግስት ይፋዊ ይቅርታ በማቅረቡ እና ከዚህ ጉዳይ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ለመፍታታ ቁርጠኝነት በማሳየቱ፣ ባንኩ በኢትዮጵያ መደበኛ ስራውን ይጀምራል" ብሏል።
ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ለመቻል ለምታደርገው ጥረት ባንኩ አስፈላጊ ነው ሲሉ በኤክስ ገለጻቸው መግለጻቸው ይታወሳል።
ልማት ባንክም በኢትዮጵያ 1.24 ቢሊዮን ዋጋ ያላቸው ፕሮጀክቶች እንዳሉት ገልጿል።