![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/06/273-165657--_167a4b199b9a66_700x400.png)
ኢትዮጵያ በየቀኑ 110 ሺህ በርሚል ነዳጅ በመጠቀም ከአፍሪካ 10ኛ ከአለም 77ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች
የአለማቀፍ የነዳጅ ፍጆታ ከኮሮና ወረርሽኝ በኋላ ጭማሪ አሳይቶ በ2024 እለታዊ የነዳጅ ፍጆታ 103 ሚሊየን በርሚል ደርሷል።
በአፍሪካ በየእለቱ 3.5 ሚሊየን በርሚል ነዳጅ ጥቅም ላይ እንደሚውል የአለማቀፉ የኢነርጂ ኤጀንሲ መረጃ ያሳያል።
እንደ ናይጀሪያ፣ አንጎላ እና አልጀሪያ ያሉ ነዳጅ አምራች ሀገራት የሚገኙባት አፍሪካ የድፍድፍ ነዳጅ ፍጆታዋ እየጨመረ መምጣቱን ቢዝነስ ኢንሳይደር አስነብቧል።
ለዚህም የግዙፍ ኢንዱስትሪዎች መስፋፋት፣ የከተሞች እድገት እና የትራንስፖርት ዘርፎች መበራከት እንደ ምክንያት ተጠቅሰዋል።
ግሎባል ፋየርፓወር ባወጣው መረጃ መሰረት በአህጉሪቱ ግብጽ ከፍተኛው መጠን ያለውን ነዳጅ በመጠቀም ቀዳሚዋ ናት፤ ካይሮ በየእለቱ 850 ሺህ በርሚል ነዳጅ በመጠቀም በነዳጅ ፍጆታዋ ከአለም 26ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
ደቡብ አፍሪካ በ601 ሺህ በርሚል ሁለተኛ፤ በአፍሪካ ቀዳሚዋ ነዳጅ አምራች ሀገር ናይጀሪያ ደግሞ ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
ኢትዮጵያ በየቀኑ 110 ሺህ በርሚል ነዳጅ በመጠቀም ከአፍሪካ 10ኛ ከአለም 77ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።