የዋጋ ጭማሪው ከዛሬ ታህሳስ 29 ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል
በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩዛሬ ማምሻውን ለመገናኛ ብዙሃ በላው መግለጫ ከዛሬ ታኅሣሥ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆነው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ መሰወኑን አስታውቋል።
በዚሁ መሰረት አንድ ሊትር ቤንዚን 101.47 ብር የሚሸጥ ሲሆን፤ የቤንዚን የመሸጫ ዋጋ ከነበረበት ከ91.14 የ10 ብር ጭማሪ ተደርጎበት ወደ 101.47 ብር ከፍ ብሏል።
አንድ ሊትር ናፍጣ ሲሸጥበት ከነበረበት 90.28 ብር የ8 ብር ጭማሪ ተደርጎበት 98.98 ብር እንዲሸጥ ተወስኗል።
እንዲሁም አንድ ሊትር ኬሮሲን 98.98 ብር፣ አንድ ሊትር የአውሮፕላን ነዳጅ 109.56 ብር እንደሚሸጥ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
አንድ ሊትር ከባድ ጥቁር ናፍጣ 105.97 ብር እንዲሁም አንድ ሊትር ቀላል ጥቁር ናፍጣ 108.30 ብር ሆኖ እንዲሸጥ መወሰኑን ሚኒስቴሩ በመግለጫው አመላክቷል።
ሚኒስቴሩ ባሳለፍነጥ ጥቅምት ወር ባወጣው መግለጫ የማክረሮ ኢኮኖሚ ማስተካከያ ተከትሎ የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ መጀመሩን ማስታወቁ ይታወሳል።
በዚሁ መሠረት የአለም የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ የነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ ማስተካከያ በየሶስት ወሩ የሚደረግ መሆኑን እ መንግሥት በነዳጅ ዓይነት የሚለያይ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ጥቅል ድጎማ ያደርጋል ማቱ አይዘነጋም።