የአፍሪካ ታዳሽ ሀይል ፈተናዎች ምን ምን ናቸው?
ለዓለም አየር ንብረት ለውጥ የአፍሪካ ሚና ጥቂት ቢሆንም አሁንም የሀይል አቅርቦት ችግር እንዳለ ነው ተብሏል
አፍሪካ ለታዳሽ ሀይል ትልቅ የኢንቨስትመንት አቅም ቢኖራትም ባለሀብቶች ግን እየተሳተፉ እንዳልሆነ ተገልጿል
የአፍሪካ ታዳሽ ሀይል ፈተናዎች ምን ምን ናቸው?
ዓለማችን ከመቼውም ጊዜ በላይ በአየር ንብረት ለውጥ እየተፈተነች ሲሆን ወደከባቢ አየር የሚለቀቀው በካይ ጋዝ መጨመር ደግሞ ለአየር ንብረት ለውጥ ዋናው ምክንያት ነው፡፡
አፍሪካ ለዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ያላት አበርክቶ ሁለት በመቶ ብቻ ቢሆንም በድርቅ፣ ጎርፍ እና ሙቀት መጨመር ምክንያት በርካታ ጉዳቶችን እያስተናገደች እንደሆነ ተገልጿል፡፡
አብዛኛው አፍሪካዊ የኤሌክትሪክ ሀይል እያገኘ አለመሆኑን ተከትሎ በርካታ የዓለማችን የሀይል ልማት ኩባንያዎች ግን በአፍሪካ የመሳተፍ ፍላጎት እንደሌላቸው ተገልጿል፡፡
ኮፕ28 የአየር ንብረት ጉባኤ የዓለማችን ጠቃሚው ጉባኤ እንደሚሆን ተገለጸ
እነዚህ ኩባንያዎች ወደ አፍሪካ መምጣት እና በታዳሽ ሀይል ላይ ኢንቨስት ማድረግ የማይፈልጉት በአፍሪካ ባለው ድህነት ምክንያት ነው ተብሏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ባለው ዝቅተኛ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣የውጭ ምንዛሬ እጥረት እና ድህነት ደግሞ ኩባንያዎቹን ወደ አፍሪካ እንዳይመጡ አድርገዋል ተብሏል፡፡
በነዚህ ምክንያቶች ሳቢያም አፍሪካ ከዓለም የሀይል ኢንቨስትመንት ውስጥ ድርሻዋ 2 በመቶ ብቻ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ደቡብ አፍሪካ በሀይል እጥረት እየተፈተኑ ካሉ የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን የሀይል አቅራቢ ኩባንያዎች ማነስ ለችግሩ ዋነኛ ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ሌላኛዋ አፍሪካዊት ሀገር ናይጀሪያ በነዳጅ ሀብቷ በአህጉሪቱ ካሉ ሀገራት መካከል ቀዳሚዋ ብትሆንም ከግማሽ በላይ ህዝቧ አሁንም ኤሌክትሪክ ተጠቃሚ አይደለም ተብሏል፡፡