ዓለም ለአየር ንብረት ለውጥ 5.9 ትሪሊዮን ዶላር ያስፈልጋል
የ2023 የቡድን 20 ጉባዔ በህንድ የተካሄደ ሲሆን፤ የአየር ንብረት ጉዳይ ከመያያ አጀንዳዎቹ ውስጥ አንዱ ነበረ።
ህንድ ባስተናገደችው የቡድኑ ጉባኤ አየር ንብረትን በተመለከተ የተሻለ ስኬት ተገኝቷል።
የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በቡድን 20 አባል ሀገራት አየር ንብረትን በተመለከተ የተደረሰው መግባባት በቂ አይደለም ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ የነዳጅ ጥቅምን ለማስቀረት ጠንካራ እርምጃ ያስፈልጋል በማለት ተናግረዋል።
በቢዝነስ ቱደይ የታተመ ሪፓርት እንደሚለው የዓለምን የሙቀት መጨመር ከሁለት ሴልሺየስ በታች፤ ከተቻለም አ1.5 ሴልሺየስ ለማድረግ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት 5.9 ትሪሊዮን ዶላር ያስፈልጋቸዋል።
ሀገራቱ በቡድ 20 እውቅና ያገኙ ብሄራዊ እቅዶቻቸውን ለማሳካት ገንዘቡ እስከ 2030 ድረስ መሰጠት አለበትም ብሏል።
በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት እስከ 2030 ድረስ ለንጹህ ኃይል ቴክኖሎጂ ተጨማሪ በየዓመቱ አራት ትሪሊዮን ዶላር ያስፈልጋቸዋል።
እርምጃው በ2050 ዜሮ ልቀት ላይ ለመድረስ ለተያዘው ውጥን የሚውል ነው።
የአየር ንብረት ገንዘብ በተለይም በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት ለመከላከልና ለመቋቋም የገንዘብ እጥረት ስለሚገጥማቸው ትልቅ መሰናክል ሆኗል።