ስምንተኛው የአፍሪካ የህዋ ሳይንስና ቴክኖሎጂ አመራርነት መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
መድረኩ የህዋ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ጥቅምን ለፖለቲካ መሪዎች፣ ለውሳኔ ሰጭዎች፣ ለተመራማሪዎች፣ ለወጣቶችና ለሴቶች ማሳወቅ፣ በአፍሪካ በህዋ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያለውን ችግር በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ፣ የአፍሪካ ሀገራት በህዋ ሳይንስ ቴክኖሎጂ በጥምረት እንዲሰሩ ማነሳሳትን አላማው ያደረገ ነው።
ለ ሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ መድረክ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ፥ የአፍሪካ ሀገራት ከጠቅላላ አመታዊ ምርታቸው 0 ነጥብ 005 ከመቶ ለዘርፉ እንዲያውሉ ጠይቀዋል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮፖሬት እንደዘገበው በመድረኩ የህዋ ሳንይንስ ቴክሎጂን በማሳደግና ከዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን የአፍሪካ ሀገራት በትብብር መስራት እንዳለባቸው ተነስቷል።
በ8ኛው የአፍሪካ የህዋ ሳይንስና ቴክኖሎጂ አመራርነት መድረክ ላይ ከአሜሪካ፣ ቻይና፣ ፈረንሳይና ጀርመንን ጨምሮ ከ18 የተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ከ 200 በላይ የዘርፉ አመራሮች፣ ምሁራን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛል።
አሜሪካ፣ ሩሲያ፣ ፈረንሳይ እና ቻይና የበጀታቸውን ከ0 ነጥብ 1 እስከ 0 ነጥብ 23 በመቶ ለህዋ ሳይንስ እንደሚያውሉት ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።