ከፍተኛ የወንጀል ምጣኔ ያለባቸው 10 የአፍሪካ ከተሞች
በደረጃው 6 ከተሞችን ያስመዘገበችው ደቡብ አፍሪካ ከአህጉሪቷ በከተሞች ከፍተኛ የወንጀል ምጣኔ ቀዳሚዋ ናት
በርካታ የወጣት ሀይሏን ከስራ ጋር ማወዳጀት የተሳናት አፍሪካ ከተሞቿ በወንጀል ምጣኔ ከአለም ቀዳሚ ሆነዋል
ከፍተኛ የወንጀል ምጣኔ ያለባቸው 10 የአፍሪካ ከተሞች
ወንጅል አለምአቀፋዊ ችግር ቢሆንም ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ልዩነት ባለባቸው የአለም ክፍሎች ምጣኔው ከፍተኛ እንደሆነ የወርልድ ፒስ ኢንዴክስ መረጃ ያመላክታል፡፡
በእርግጥ በበለጸጉት ሀገራትም ያለው ምጣኔ ቀላል የሚባል አይደለም። ባለግዙፍ ኢኮኖሚዋን አሜሪካ ለአብነት ብናነሳ በሀገሪቱ በየ 24.6 ሰከንድ ልዩነት አስከፊ ወንጀል የሚፈጸም ሲሆን በ30.5 ደቂቃው ደግሞ አንድ ሰው ይገደላል። በየ 3.9 ደቂቃው አንድ ሴት ትደፈራለች፤ በ39.0 ሰከንድ ልዩነት ንብረት ላይ ያነጣጠረ ወንጀል ይፈጸማል፡፡
የፍትሀዊ ሀብት ክፍፍል ያልሰፈነባት በዜጎች መካከል ሰፊ የኢኮኖሚ ልዩነት የሚንጸባረቅባት አፍሪካ በወንጀል ምጣኔ ከሚጠቀሱ አለም ክፍሎች መካከል ቀዳሚዋ ናት፡፡
በርካታ የወጣት ቁጥር እና ሰፊ የስራ አጥነት እንዲሁም የዋጋ ንረት የተጫነው ኢኮኖሚ በሚመሩ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ንብረት ዝርፍያ እና ስርቆትን የመሳሰሉ ኢኮኖሚያዊ ወንጀሎች ህይወትን ለማስቀጠያ እና በአቋራጭ የተሻለ ስፍራ ለመድረስ በሰፊው በአማራጭነት እየተወሰዱ ይገኛሉ፡፡
በከተማ እና በበርካታ ህዝብ በሚኖርባቸው አካባቢዎች የሚደጋገሙት ወንጀሎች ከግለሰብ እስከተደራጁ የወንጀል ቡድኖች የሚፈጸሙ ናቸው፡፡
ወርልድ ፒስ ኢንዴክስ ከፍተኛ የወንጀል ምጣኔ ያለባቸው 10 የአፍሪካ ከተሞች በሚል ባወጣው ዝርዝር ውስጥ ደቡብ አፍሪካ 6 ከተሞቿን በተርታ በማስመዝገብ በአለም ቀዳሚዊ ናት፡፡
በአፍሪካ የወንጀል ምጣኔ ከከፋባቸው ከተሞች መካከል በቀዳሚነት የምትገኝው ፒተርማሪትዝበርግ በ82.5 የወንጀል ምጣኔ ከአለም አቀፍ ደረጃም በአንደኛነት ትገኛለች፡፡