የዜጎቻቸው የአዕምሮ ጤና ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል የተባሉ የአፍሪካ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
የግሎባል ማይንድ ፕሮጄክት ‘የዓለም የአእምሮ ሁኔታ’ መሰረት የአፍሪካ ሀገራት ደረጃን ይፋ አድርጓል
ሪፖርቱ ከኮሮና ወረርሽኝ ወዲህ የሰዎች የአዕምሮ ሁኔታ እያሽለቆለቆለ መምጣቱን አመላክቷል
በአፍሪካ ውስጥ ያለው የአእምሮ ጤና ሁኔታ በተለያዩ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ሁኔታዎች ለጉዳት የተጋለጠ እና ውስብስብ እንደሆነ ይነገራል።
ዓለም ከከፍተኛ የኑሮ ውድነት እስከ ወረርሽኞች፣ ከድርቅ እስከ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ድረስ ብዙ ጉዳዮችን እያስተናገደች ሲሆን፤ የአፍሪካ ሀገራትም የዚሁ ሰለባ ናቸው።
የግሎባል ማይንድ ፕሮጄክት ከኮሮና ወረርሽኝ ወዲህ ‘የዓለም የአእምሮ የጤና ሁኔታ’ የሚያሳይ የጥናት ውጤት ከሰሞኑ ይፋ አድርጓል።
በሳፒየን ላብስ በተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው እድሜያቸው ከ65 በላይ የሆኑት የተረጋጋ የአእምሮ ጤንነት ያሳዩ ሲሆን፤ በወጣትነት የእድሜ ክልል የሚገኙ በተለይም ከ35 ዓመት በታች የሆኑት ላይ የአዕምሮ ጤና ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሱ ናቸው።
ሳፒየን ላብስ ከ27 ሺህ 969 ሰዎች ላይ በሰበሰበው መጠይቅ አሁን ላይ እድሜያቸው ከ18 እስከ 24 የሆኑ ወጣት ትውልዶች የመጀመሪያ ስማርት ስልካቸውን እንደተቀበሉ የአድምሮ ጤና ሁኔታው እየተዛባ መሄዱን እንደሚያሳይ ለይቷል።
በተጨማሪም በብዛት በፋበሪካ የተቀነባበሩ ምግቦችን አብዝተው የሚወስዱ ሰዎች የአእምሮ ጤና ሁኔታ ዝቅተኛ ሆኖ መገኘቱንም ጥናቱ አመላቷል።
በጥናቱ የተለየው ሶስተኛ የአእምሮ ጤና ሁኔታ የመቀነስ ምክንያት በቤተሰብ መካከል ያለው ግንኙነት ሲሆን፤ በጥናቱ ከቤተሰቦቻው ጋር ዝቅተኛ የሆነ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች ከቤተሰቦቻው ጋር የጠበቀ ግንኙነት ጋላቸው ጋር ሲነጻጸሩ የአእምሯቸው ጤና ሁኔታ ዝቅተኛ ሆኖ ተገኝቷል ነው የተባለው።
ሪፖርቱ በየሀገራቱ ያሉ ሰዎች የአእምሮ ጤነንት ሁኔታ እና ጥራት ግምት ውስጥ በማስገባት የአፍሪካ ሀገራትን ደረጃ ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሰረት በአፍሪካ ከአእምሮ ሁኔታ ጋር መሰረት የዜጎቻቸው የአዕምሮ ጤና ዝቅተኛ የሆነባቸው የአፍሪካ ሀገራት እና የአእምሮ ጤና መለኪያ መስፈርት በመቶኛ እንደሚከተለው ቀርቧል፤
1. ደቡብ አፍሪካ 50 በመቶ
2. ግብጽ 55 በመቶ
3. አልጄሪያ 64 በመቶ
4 ሱዳን 64 በመቶ
5 ሞሮኮ 64 በመቶ
6. አንጎላ 64 በመቶ
7. ቱኒዚያ 67 በመቶ
8. ካሜሮን 67 በመቶ
9. ኮት ዲቯር 69 በመቶ
10. ሞዛምቢክ 70 በመቶ