ደስተኛ ህዝቦች ያላቸው 10 የአፍሪካ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
የግሎባል ማይንድ ፕሮጄክት ‘የዓለም የአእምሮ ሁኔታ’ መሰረት በማድረግ የሀገራት የደስታ ደረጃን ይፋ አድርጓል
ሪፖርቱ ከኮሮና ወረርሽኝ ወዲህ የሰዎች የአዕምሮ ሁኔታ እያሽለቆለቆለ መምጣቱን አመላክቷል
ዓለም ከከፍተኛ የኑሮ ውድነት እስከ ወረርሽኞች፣ ከድርቅ እስከ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ድረስ ብዙ ጉዳዮችን እያስተናገደች ነው።
እናም በእነዚህ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ደስታን ፈልጎ ማግኘት በአለም አቀፍ እና በአፍሪካ ሀገራት ትልቅ ግብ ሆኗል።
የግሎባል ማይንድ ፕሮጄክት ‘የዓለም የአእምሮ የጤና ሁኔታ’ መሰረት በማድረግ ዓመታዊ የሀገራት የደስታ ሁኔታ እና ያለበትን ደረጃ ይፋ እርጓል።
በግሎባል ማይንድ ሪፖርት መሰረትም በዓለም ላይ ከተከሰተው ከኮሮና ወረርሽኝ ወዲህ የሰዎች የአዕምሮ የጤንነት ሁኔታ እያሽለቆለቆለ መምጣቱን አመላክቷል።
ሪፖርቱ አፍሪካን ጨምሮ 9 አሁጉሮች ላይ ከሚገኙ በ71 ሀገራት ውስጥ ከሚኖሩ ከ500 ሺህ በላይ ግለሰቦች የተሰጡ ምላሾችን መሰረት በማድረግ የተዘጋጀ ነው።
በዚህም መሰረት ከ2021 ወዲህ በዓለም ዙሪያ ያለው የሰዎች አእምሮ ደህንነት ሁኔታ በዙም መለዋወጥ የማይታይበት በሆኑ ተመላክቷል።
ሪፖርቱ በየሀገራቱ ያሉ ሰዎች የአእምሮ ጤነንት ሁኔታ እና ጥራት ግምት ውስጥ በማስገባት የአፍሪካ ሀገራትን ደረጃ ይፋ አድርጓል።
በአፍሪካ ከአእምሮ ሁኔታ ጋር መሰረት ደስተኛ የሆኑ ሀገራት እና የአእምሮ ጤና መለኪያ መስፈርት በመቶኛ
1ኛ ታንዛኒያ 88 በመቶ
2ኛ ናይጄሪያ በ83 በመቶ
3ኛ ዚምባዌ በ74 በመቶ
4ኛ ኬንያ 72 በመቶ
5ኛ ዲ.አር.ኮንጎ 71 በመቶ
6ኛ ሞዘሚክ 70 በመቶ
7ኛ ኮት ዲቯር 69 በመቶ
8ኛ ካሜሮን 67 በመቶ
9ኛ ቱኒዝያ 67 በመቶ
10ኛ አንጎላ 64 በመቶ