ጉቦ የሚቀበሉ ፖሊሶች የተበራከቱባቸው 10 የአፍሪካ ሀገራት
በአፍሪካ ሙያዊ ግዴታቸውን ለመወጣትና ወንጀለኛን ለመደበቅ ጉቦ የሚጠይቁ ፖሊሶች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ጥናት አሳይቷል
ጥናቱ ፖሊሶች ሙያዊ መርህና የዜጎችን መብት አክብረው እንደሚንቀሳቀሱ የሚያምኑ አፍሪካውያን 30 በመቶው ብቻ ናቸው ብሏል
አፍሮባሮሜትር የተሰኘው ድረገጽ በ39 ሀገራት የፖሊሶችን የሃይል አጠቃቀም፣ የሙስና እና ሌሎች ወንጀሎች ተጋላጭነት በተመለከተ የዳሰሳ ጥናት አድርጓል።
ከ2021 እስከ 2023 የተካሄደው ጥናት ፖሊሶች ሙያዊ መርህና የዜጎችን መብት አክብረው እንደሚንቀሳቀሱ የሚያምኑ አፍሪካውያን 30 በመቶው ብቻ ናቸው ብሏል።
54 በመቶ አፍሪካውያን ከፖሊሶች ድጋፍ ለማግኘት ቀላል መሆኑን ሲገልጹ፥ 36 በመቶው ጉቦ መክፈል ግዴታ ነው ማለታቸውም በጥናቱ ተመላክቷል።
ይህም ፖሊሶች በህብረተሰቡ ዘንድ ታማኝነታቸውን እየሸረሸረ በሙያው ላይም አሉታዊ አመለካከት እንዲዳብር ማድረጉ ነው የተገለጸው።
በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት የወንጀል ጥቆማዎችንና ድንገተኛ አደጋን ሪፖርት አድርጎ ፈጣን የፖሊስ ምላሽ ለማግኘት ብሎም በወንጀል የሚያስጠረጥር ጉዳይን ለማስቀረት ጉቦ መክፈል እየተለመደ መምጣቱን ነው የአፍሮባሮሜትር የዳሰሳ ጥናት ያሳየው።
ጉቦ የሚቀበሉ ፖሊሶች የተበራከቱባቸው 10 የአፍሪካ ሀገራትን ይመልከቱ፦