ልዩልዩ
የአፍሪካ ሀገራት እስካሁን ከ26 ሚሊየን በላይ የኮቪድ 19 ክትባቶችን መቀበላቸው ተገለፀ
28 የአፍሪካ ሀገራት በኮቫክስ ጥምረት አማካኝነት ከ16 ሚሊየን ዶዝ በላይ ክትባቶችን ተረክበዋል
7 ሚሊየን 272 ሺህ 148 ዶዝ ክትባቶች በአግባቡ ለሰዎች መሰጠታቸውንም ሲ.ዲ.ሲ አፍሪካ አስታውቋል
የአፍሪካ ሀገራት እስካሁን ከ26 ሚሊየን በላይ የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባቶችን መቀበላቸውን የአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል (አፍሪካ ሲ.ዲ.ሲ) አስታወቀ።
ሀገራቱ የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባቶችን በኮቫክስ ጥምረት አማካኝነት እና ከጥምረቱ ውጪ ከሀገራት ጋር ባላቸው የሁለትዮሽ ሽምምነቶችን በመጠቀም ማግኘታቸውንም አስታውቋል።
በዚህም መስረት 28 የአፍሪካ ሀገራት በኮቫክስ ጥምረት አማካኝነት 16 ሚሊየን 245 ሺህ 560 ዶዝ ክትባቶችን መረከባቸውን የአፍሪካ ሲ.ዲ.ሲ መረጃ ያመለክታል።
ከእነዚም ውስጥ 7 ሚሊየን 272 ሺህ 148 ዶዝ ክትባቶች በአግባቡ ለሰዎች እንደተሰጡም አፍሪካ ሲ.ዲ.ሲን ጠቅሶ ሲ.ጂ.ቲ.ኤን ዘግቧል።
በተጨማሪም 18 የአፍሪካ ሀገራት ከኮቫክስ ጥምረት ከሀገራት ጋር ባላቸው የሁለትዮሽ ግንኙነትን በመጠቀም 10 ሚሊየን 34 ሺህ 220 የኮቪድ መከላከያ ክትባችን መረከባቸውም ተመላክቷል።
እንዲሁም ኤም.ቲ.ኤን ለአፍሪካ ሀገራት የክትባት ድጋፍ ባዘጋጀው የ25 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ማእቀፍ አማካኝት 9 የአፍሪካ ሀገራት 723 ሺህ ክትባቶችን መረከባቸውን አፍሪካ ሲ.ዲ.ሲ አስታውቋል።