ልዩልዩ
በአፍሪካ ጠንካራ ወታደራዊ ሃይል ያላቸው 10 ሀገራት
ግሎባል ፋየርፓወር በአፍሪካ ከፍተኛ ወታደራዊ በጀት የያዙና ጠንካራ ሰራዊት የገነቡ ሀገራትን ይፋ አድርጓል
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ 5ኛ ከአለም ደግሞ 49ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች
የአለም ሀገራት ወታደራዊ አቅማቸውን ለማሳደግ በየአመቱ የሚይዙትን በጀት እያሳደጉ ነው።
የሀገራት ወታደራዊ እንቅስቃሴን የተመለከቱ መረጃዎችን በማጋራት የሚታወቀው ግሎባል ፋይበርፖወር ባወጣው ዘገባ መሰረት፣ አሜሪካ፣ ቻይና፣ ሩሲያ፣ ህንድ እና ሳኡዲ አረቢያ ከፍተኛ ወታደራዊ በጀት በመያዝ እስከ5ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።
ድረገጹ የ145 ሀገራት ወታደራዊ አቅም በተለያዩ መስፈርቶች በመመዘንም አስፈሪ ሰራዊት መገንባት የቻሉ ሀገራትን ዝርዝር አውጥቷል።
በ2024 በአፍሪካ ከፍተኛ ወታደራዊ በጀት በመያዝ አልጀሪያ (21.6 ቢሊየን ዶላር) ቀዳሚዋ ናት፤ ሞሮኮ፣ ግብጽ እና ናይጀሪያ ይከተላሉ።
ጠንካራ ሰራዊት በመገንባት ደግሞ ግብጽ ከአህጉሩ 1ኛ ከአለም ደግሞ 15ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
ኢትዮጵያም በ2024 በጀት አመት 888 ሚሊየን ዶላር ለመከላከያ ሃይሏ እንደያዘች ይታመናል ያለው ግሎባል ፋየርፓወር፥ ጦሯ በአፍሪካ 5ኛ በአለም ደግሞ 49ኛ ደረጃ ላይ መቀመጡን ገልጿል።
በ2024 ጠንካራ ወታደራዊ ሰራዊት ያላቸው 10 ሀገራት ዝርዝርን ይመልከቱ፦