የዓለም ወታደራዊ በጀት በታሪክ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል
ከወራት በፊት ፍጻሜውን ያገኘው የፈረንጆቹ 2022 ዓመት በዓመታዊ ወታደራዊ ታሪክ ከፍተኛ በጀት የተመደበበት ዓመት ሆኗል።
በአጠቃላይ ዓለም 2240 ቢሊዮን ዶላር ለወታደራዊ ጉዳዮች ቢሊዮን ዶላር እንደተበጀተ የስዊድኑ ዓለም አቀፍ የሰላም ጥናት ማዕከል አስታውቋል።
የዓለም ልዕለ ሀያል የሆነችው አሜሪካ 877 ቢሊዮን ዶላር ስትመድብ ቻይና ደግሞ 292 ቢሊዮን ዶላር በመመደብ ሁለተኛዋ ሀገር ሆናለች።
ጦርነት ውስጥ ያሉት ሩሲያ እና ዩክሬን ወታደራዊ በጀታቸውን ያሳደጉ ተጨማሪ ሀገራት እንደሆኑ ተገልጻል።
ዩክሬን 44 ቢሊዮን ዶላር በመመደብ በ2021 ዓመት ለመከላከያ ከበጀተችው ጋር ሲነጻጸር የ640 በመቶ ጭማሪ አሳይታለች።
ጦርነት እያስተናገደ ያለው አውሮፓ ከሌሎች አህጉራት ጋር ሲነጻጸር ወታደራዊ በጀት ጭማሪ ካሳዩ ሀገራት መካከል ቀዳሚው ነው ተብሏል።