በ2024 በአፍሪካ በጣም ቀርፋፋ የሞባይል ኢንተርኔት (ዳታ) ያላባቸው ሀገራት የትኞቹ ናቸውʔ
በአፍሪካ የኢንተርኔት ተደራሽነት እያደገ ቢመጣም የፍጥነቱ ነገር ግን አስቸጋሪ ነው
ሱዳን፣ አንጎላና ካሜሮን በቀርፋፋ የሞባይል ኢንተርኔት ቀዳዎቹ ናቸው ተብሏል
በአፍሪካ የኢንተርኔት ተደራሽነት እየጨመረ የመጣ ቢሆንም፤ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎተን በተለይ ከከተማ ውጪ ላይ ማግኘት በጣም አስቸጋሪ እንደሆነ ይታወቃል።
በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ያለው ቀርፋፋ የሞባይል ኢንተርኔት (ዳታ) ችግር ውስብስብ ቢሆንም፤ በርካታ ችግሮች እንደሚስተዋሉበትም ነው የሚነገረው።
በአፍሪካ ከተሞች አካባቢ የተሻለ የፍጥንት ያለው ኢንተርኔት ማግኘት ቢቻልም፤ በገጠራማ አካባቢ ያሉ ሰዎች ግን ይህንን ለማግኘት አልታደሉም።
ቀርፋፋ የሞባይል ኢንተርኔት ምርታማነትን እና የስራ ፈጠራን እንዲሁም የንግድ ስራዎች እድገትን በተጨማሪም በትምህርት እና ጤና ዘርፍ ላይ ከፍተኛ እንቅፋት መሆናቸውም ነው የሚነገረው።
የሞባይል ኢንተርኔት መንቀራፈፍ የአብዛኛው የአፍሪካ ሀገራት ችግር እንደሆነም ስፒድ ቴስት ግሎባል የ2024 የመጀመሪያ ወር ሪፖርቱ ላይ አመላክቷል።
የስፒድ ቴስት ጎላባል በሀገራት ያለውን የሞባይል ኢንተርኔት ፍጥነት በሜጋ ባይት በሰከንድ እና በዓለም ላይ ያላቸውን ደረጃ አስቀምጧል።
በሪፖርቱ መሰረትም በኢትዮጵያ ያለው የሞባይል ኢንተርኔት ፍጥነት በአማካይ 29.70 ሜጋ ባይ በሰከንድ ነው ያለ ሲሆን፤ በዚህ ከዓለም 84ኛ ደረጃ ላይ እንደሚትገኝ አስታውቋል።
በግሎባል ስፒድ ቴስት ሪፖርት መሰረት ከአፍሪካ በጣም ቀርፋፋው የሞባይል ኢንተርኔት ያለባት ሀገር ሱዳን ስትሆን፤ በሱዳን በ4.82 ሜጋ ባይት በሰከንድ ፍጥነት ከአፍሪካ 1ኛ፤ ከዓለም 142ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
በአንጎላ 10.89 ሜጋ ባይት በሰከንድ የሞባይል ኢንተርኔት ፍጥነት ያለባት ሲሆን፤ በዚህ ከአፍሪካ 2ኛ ከዓለም ደግሞ 136ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
በቀርፋፋ የሚባይል ኢንተርኔት ከአፍሪካ 3ኛ ከዓለም 129ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ካሜሮን ስትሆን፤ በሀገሪቱ ያለው የሞባይል ኢንተርኔት ፍጥነት 13.97 ሜጋ ባይት በሰከንድ ነው።
ሊቢያ 15.09 ሜጋ ባይት በሰከንድ ፍጥነት ከአፍሪካ 4ኛ ከዓለም 137ኛ ላይ ስትቀመጥ፣ ጋና 16.43 ሜጋ ባይት ሰበከንድ ፍጥነት ከአፍሪካ 5ኛ፣ ከዓለም 125ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
ዛምቢያ፣ ሞዛምቢክ፣ ዲ.አር.ኮንጎ፣ አልጄሪያ እና ሶማሊያም ከአፍሪካ ቀርፋፋ የሞባይል ኢንተርኔት ያለባቸው ሀገራት በመባል ከ6ኛ እስከ 10ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።